በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
📖መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ላንብብ📖
ክፍል ፭(5)
#የመጽሐፍ #ቅዱስ #አተረጓጎም
ዛሬ የመጽሐፍ ቅዱስን አተረጓጎም እናያለን።
የምናነበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በየትኛው የአተረጓጎም ስልት እንደተጻፈ ካላወቅን የምናነበውን ንባብ ላንገነዘበው እንችላለን።መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና አራት የትርጉም ዓይነቶች አሉት፦
፩. የነጠላ ትርጉም
፪. ምሳሌያዊ ትርጉም
፫. ምስጢራዊ ትርጉም
፬. ሕይወት ተኮር ትርጉም ናቸው
ሁሉንም እስኪ በተራ እንያቸው
፩. #ነጠላ #ትርጉም
ነጠላ ትርጉም የምንለው ንባቡን በቀጥታ ወስደን ያለምንም ዝርዝር የምንጠቀምበትን ነው! ለምሳሌ፦
፩. "እግዚአብሔር በመጀመርያ ሰማይና ምድርን ፈጠረ" ኦ. ዘፍ ፩፡፩
፪. "ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ" ማቴ ፳፮፡፵፩
፪. #ምሳሌያዊ #ትርጉም
ምሳሌ በዕብራይስጥ "ማሻል" ይባላል።ምሳሌያዊ ትርጉም አንድ ነገርን የበለጠ ለመግለፅ ይረዳል።ለምሳሌ፦
፩. "እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ" ዮሐ ፩፡፳፱ ኢየሱስ ክርስቶስ በበግ መመሰሉን እንመለከታለን
፪. እስራኤላውያን በወይን ቦታ እንደተመሰሉ በ ት. ኢሳ ፭፡፩-፪ የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለት መመሰል ት. ዳን ፪፡፴፬
፫. #ምስጢራዊ #ትርጉም
ምስጢራዊ ትርጉም የተሰወረ የተደበቀ ነገር የያዘ ላይ በላይ የማይታይ ማለት ነው።መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ሂደት ውስጥ ምስጢሩን ማግኘት ወይም መረዳት ካልተቻለ መልዕክቱን መጨበጥ አይቻልም።ምስጢራዊ ትርጉም ጥሬ ዘሩን ወይም ንባቡን ብቻ ሳይከተል ንባቡን ሳይጠብቅ ምስጢሩን በዋናነት ጠብቆ የሚተረጎም ነው።
"በበሰሉት መካከል ጥበብን እንናገራለን ተሰውሮ የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምስጢር እንናገራለን" ፩ቆሮ ፪፡፮-፯
በምስጢራዊ ትርጉም ውስጥ ሊገለጡ የሚችሉ ምስጢራት፣ያልተገለጡ ምስጢራት፣ ወደፊት የሚገለጡ ምስጢራት፣ምንም ሊገለጡ የማይችሉ ምስጢራት እንዳሉ ማወቅ አለብን። በመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ ሲነበብ ይህንን መረዳት አለብን።
፬. #የሕይወት #ትርጓሜ
የሕይወት ትርጓሜ የምንለው መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብ ሰው በሕይወቱ ውስጥ የሚሰጠው ትርጉም ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ የምናገኘውን የሕይወት ለውጥ ትህትና፣ሰላም፣ደስታ፣ፍቅር፣ርህራሄ...ያጠቃልላል።
ቃሉን በሕይወታችን እንድንተገብር የርሱ መልካም ፍቃድ ይሁን
በቀጣይ
📖የመጽሐፍ ቅዱስ ዘይቤና
📖መጽሐፍ ቅዱስን በጊዜና በሰዓት ከፋፍሎ የማንበብ ስልት እናያለን
https://t.me/Abalibanos333
ይቀጥላል