ኦቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ መደበኛ ስርጭቱን አቋረጠ
ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (ኦቢኤስ) ቴሌቪዥን ጣቢያ መደበኛ ስርጭቱን ማቋረጡን አስታውቋል። ጣቢያው ስርጭቱን ያቋረጠው የሳተላይት ኪራይ ወጪውን መቋቋም ባለመቻሉ ነው ተብሏል፡፡
ኦቢኤስ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት፤ ከመስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የሳተላይት ስርጭቱን እንዳቋረጠ ገልጿል። በማያያዝም፣ ስርጭቱን የማቋረጡ ምክንያት የዶላር የምንዛሪ ዋጋ ላይ የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ፣ የሳተላይት ኪራይ ወጪ በመጨመሩ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ተከታታዮቹ በተለያዩ ማሕበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ላይ ድጋፋቸውን መግለጻቸውን በምስጋና የጠቀሰው ኦቢኤስ፤ የጣቢያውz ስራ አመራር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሳተላይት ስርጭት ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ እንደሚገኝ በዚሁ መልዕክት ላይ አብራርቷል፡፡ “ድጋፍ እያደረጉልኝ ነው” ላላቸው ወገኖችም ምስጋናውን አቅርቧል።
ኦቢኤስ የሳተላይት ስርጭቱ ቢቋረጥም፣ በዩቲዩብ ቻናሉ ግን መደበኛ ፕሮግራሞቹን ለተመልካቾቹ እያደረሰ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
ቴሌቪዥን ጣቢያው የሪፍትቫሊ ዩኒቨርስቲና ሌሎች የንግድ ተቋማት ባለቤት በሆኑት አቶ ድንቁ ደያስ ድጋፍ መቋቋሙ የሚታወቅ ነው።
@Addis_Reporter