አሚጎስ ከ101 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
• የማህበሩ ጠቅላላ ሃብት 3ቢ.ብር ደርሷል
አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የህብረት ሥራ ማህበር፣ በ2016 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 145 ሚሊዮን ብር ማትረፉንና ከ101 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
የማህበሩ አባላት የትርፍ ክፍፍል ድርሻ 53 i በመቶ ነው ተብሏል፡፡
የህብረት ሥራ ማህበሩ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ታሕሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም፣ 11ኛ የባለአክስዮኖች ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
የማህበሩ አባላት በተገኙበት ለግማሽ ቀን በተካሄደው በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም የአሚጎስ ጠቅላላ ሃብት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡
አሚጎስ በዛሬው ጉባኤው የኅብረት ስራ ማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች የመረጠ ሲሆን፤ በቀጣይ ያቀዳቸው ሰፋፊ ስራዎችም ቀርበዋል።
የዛሬ 12 ዓመት በሦስት ዓይን ገላጭ መሥራቾች ተጀምሮ ዛሬ ወደ 10ሺ የሚጠጉ አባላትን ያፈራው የህብረት ሥራ ማህበሩ፤ ወደ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ አጠቃላይ ካፒታል ያለው ሲሆን፤ ከ120 በላይ ሰራተኞች ይዞ በተለያዩ የክልል ከተሞች ቅርንጫፎቹን በማብዛት ተደራሽነቱን እያሰፋ እንደሚገኝ ከማህበሩ የተገኘ መረጃ ይጠቁማል፡፡u