ግብር ከፋዩ በእጁ ያለው ማንዋል ደረሰኝ ከየካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ ስለማይው አዲሱን ደረሰኝ ከወዲሁ እንዲያሳትም ጥሪ ቀረበ ።
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የልደታ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ የኃላወርቅ ለማ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት " አሁን አገልግሎት እየሰጠ ያለው ማንዋል ደረሰኝ ከየካቲት 02 / 2017 ዓ.ም ጀምሮ ጥቅም ላይ ስለማይውል ግብር ከፋዩ ይህን ተገንዝቦ ከወዲሁ አሳውቆ ወደ ህትመት እንዲገባ አሳስበዋል ።
ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ከደረሰኝ ህትመት ጋር ተያይዞ እስካሁን የሰራቸው ስራዎች በተመለከተ ሀላፊዋ እንደገለፁት በአካል ሲመጡ ለግንዛቤ የተዘጋጁ ብሮሸሮች፣ በራሪ ወረቀት በመስጠት በቴሌ አጭር መልዕክት በመላክ ፣ በቅርንጫፉ ማህበራዊ የቴሌግራም ቻናል በመጠቀም ጭምር እንዲያውቁ መደረጉን ተናግረዋል
ከገቢ አሰባሰብ አንፃርበበጀት አመቱ በስድስት ወራት 1693,28ቢሊየን ብር ለመሠብሰብ ታቀዶ፣ 1701.72 ቢሊየን ብር የተሰበሰበ ሲሆን የዕቅዱን 100.5 ፐርሰንት ማሳካት መቻሉን ጠቁመዋል።
ግብርከፋዮች ጊዜ አለን በሚል መዘናጋት ደረሰኝ ሳያሳትሙ ለአላስፈላጊ እንግልትና ቅጣት እንዳይዳረጉ ከወዲሁ አሳውቀው ደረሰኝ እንዲያሳትሙ ሀላፊዋ መልዕክታቸውን አስተላልፈውል ።