ክፍል 3 (የመጨረሻ ክፍል)
11. ሚዲያ በልጆች የስሜት እና በጤናማ ማህበራዊ ግንኙነት መዳበር ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል/IMPACT on SOCIAL-EMOTIONAL DEVELOPMENT/
የስሜት መዳበር እንደሌሎች የመዳበር ዘርፎች በሂደት የሚያድግ ሲሆን እደገቱ ስኬታማ እንዲሆን የቤተሰብ፣ መምህራን እና የሊሎችም ሚና በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የስሜት መዳበር በአእምሮ መዳበር አማካኝነት የሚከሰት ለውጥ ሲሆን የራስን ስሜት መረዳትና መቆጣጠር መቻልን እንዲሁም ለሌሎች ርህራሄ እና ፍቅር እንዲኖረን የሚዳርግ ነው፡፡ ይህ እድሜ ሲጨምር የበለጠ እየዳበረ የሚሄድ የመዳበር ዘርፍ ነው፡፡ ነገር ግን ለእደገቱ ወሳኝ የሆነ ሁኔታ እስካልተፈጠ ድረስ ለውጡ የሚታሳብ አይደለም ይሉቁንም የራሳቸውን ስሜት ብቻ የሚያስቀድሙ እና ለሌሎች ደንታ የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በዚህ ረገድ ሚዲያ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ሲሆን ይህም የሚሆን ለረዥም ሰዓታት በትዕንት መስኮት ጊዜን ማሳለፍ በእውነተኛው ህይወት የሰዎችን ስሜትና ሁኔታ ለመመልከት ጊዜ እንዳይኖራቸው ስለሚያደርግ ነው፡፡
የልጆች ስሜት አወንታዊ በሆነ መንገድ እንዲደብር ከሰዎች ጋር መገናኘትና መስተጋብር መፍጠር አስፈላጊ ነው። ሚዲያ በልጆች ስሜታዊና ማህበራዊ መዳበር ላይ የሚዳርሰው አሉታዊ ተፅዕኖ በተመለከተ በስድሰተኛ ክፍል ተማሪዎች የሰዎችን በፎቶና ቪዲዮ ስሜታቸውን የመረዳት ችሎታ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ ከነዚህ ተማሪዎች የተወሰኑት ለአምስት ቀናት ትዕይንቶችን በሚዲያ መስኮት እንዲመለከቱና የተቀሩት ደግሞ ምንም አይነት ትዕይንት በሚዲያ እንዳይከታተሉ በማደረግ ያላቸወን የሰዎች ስሜት የመረዳት ችሎታ ለመለካት የተቻለ ሲሆን ውጤቱ እንደሚያሳየው ለአምስት ቀናት ሚዲያ ያልተከታተሉ ልጆች ከጥናቱ በፊት ከነበራቸው የሰዎችን ስሜት የመረዳት ችሎታ የበለጠ መሻሻል ሲያሱ ለአምስት ቀናት ሚዲያ የተከታተሉት ግን በተቃራኒው በፊት ከነበራቸው ስሜትን የመረዳት ችሎታ ያነሰ ሁኖ ተመዝግቦል፡፡ ከሚዲያ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ከሰዎች ጋር የሚኖርን የርስበርስ ግንኙነት እንዲቀንስ በማድረግ በሰዎች ላይ የስሜት ምልክቶችን መከታተል እንዳይችሉ እና የሰዎችን ስሜት የመረዳት ችሎታም እንዲቀንስ የሚያደርግ ሲሆን ወጤቱም የስሜት መዳበርን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጎዳ የጥናቱ ተመራማሪዎች አስተውቀዋል፡፡
ሚዲያ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ እና ለማስቀረት ወላጆች ሊተገብሯቸው የሚገቡ ነገሮች
ሚዲያ በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስና ያለውን አወንታዊ አስተዋፅኦ ለመጨመር ወላጆች ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው በጉዳዩ ሰፊ ጥናት ያደረጉ ሙህራኖች ያሳስባሉ፡፡ ነገር ግን የሚዲያን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስና አወንታዊ አስተዋፅኦ የማሳደግ ተግባር በወላጆች ብቻ የሚሳካ ተግባር ሳይሆን የመምህራን፣ የሚዲያው ባለቤቶች፣ የመንግስት ፖሊሲ አውጭዎችና አስፈፃሚዎችን ቁርጠኝነት የሚፈልግ ነው፡፡ ከዚህ በታች የቀረቡትን ምክሮች ወላጆች በመተግበር ሚዲያ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ በመቀነስ አወንታዊ አስተዋፅኦውን ለመጨመር የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል፡፡
1. ልጆች በተለይ እድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የሚመለከቱበትን ጊዜ መቀነስ
2. የኤሌክትሮኒክስ መጫወቻዎችን መቀነስና በምትኩ ሌሎች መጫወቻዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ
3. የተለያዩ የፈጠራ ችሎታን የሚያሳድጉ መጫወቻዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት ለምሳሌ የሚገጣጠሙ፣ የሚደረደሩ እና በተግባር ልጆች እያዩና እየነካኩ ሊጫወቱባቸው የሚያስችሉ መጫወቻዎች
4. በምግብ ሰዓት ቴሌቭዥን መዝጋት እንዲሁም ሌሎች ሚዲያዎችንም እንዳይጠቀሙ ማድረግ መረሳት የለበትም
5. በመተኛ ክፍሎቻቸው ልጆች ቴሌቭዥን ፣ኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳያገኙና እንዳይጠቀሙ ማድረግ።
6. ልጆችን ከኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ውጭ የሆኑ የመዝናኛ ተግባራትን ማለትም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚጫወቱባቸው፣ የአእምሮ ተግባራትን የሚፈልጉ ጨዋታዎች እና ተግባራት በመስራት እንዲያዘወትሩ ማበረታታት
7. ለልጆች እድገት አስፈላጊ የሆኑ እና ትምህርት ሰጭ የሆኑ የቴሌቪዝን ፕሮግራሞች በመምረጥ አንድላይ ከልጆች ጋር ሁነው መመልከት የሚገባ ሲሆን በሚመለከቱበት ጊዜም ልጆች የተመለከቱትን ነገር ምን ያህል እንደተረዱት መጠየቅ፣ ማብራሪያ መስጠት ያስፈልጋል፡፡
8. በሚዲያ አጠቃቀማቸው ወላጆች ለልጆች ጥሩ አርዓያ እና ምሳሌ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ልጆችን በቤት ውስጥ አስቀምጦ የአዋቂ ይዘት ያላቸው ፊልሞች፣ፕሮግራሞች የመመልከት ሁኔታ በየቤቱ ይስተዋላል ፡፡ ይህን በማስወገድ ተገቢ ወደሆኑ ተግባራት ማምራትና ማከናወን ይገባል ፡፡ ለምሳሌ ማንበብ፣ የተለያዩ የወረቀት ስራዎችን መስራት ወዘተ ይህን ልጆች በሚመለከቱበት ጊዜ እነሱም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይፈልጋሉ ፡፡
9. ወላጆች የራሳቸውን የሚዲያ አጠቃቀም መገደብ በምትኩ ለልጆችም ጊዜን በመመደብ የተለያዩ ታሪኮችን፣ ተረቶችን ማውራትና የልጆችን አዕምሮ የሚያሳድጉ የተለያዩ ጥያቄዎችን እና ተግባራትን መስጠት ይገባል፡፡
10. ወላጆች ከጎረቤቶቻቸው እና ከአካባቢ ሰዎች ጋር ስለልጆቻቸው የሚዲያ አጠቃቀም፣ የሚዲያ ተፅዕኖ በማንሳት መወያየትና የጋራ የሆነ መግባባት ላይ መድረስ ይገባቸዋል፡፡ ምክኒያቱም ልጆች በቤታቸው የሚያዩት ፊልሞች ቢከለከሉ ሌላኛው ቤት ውስጥ በመሄድ የማየት ሁኔታ ስለሚኖር ተመሳሳይ የሆነ መግባባት ላይ መድረስ ይገባቸዋል፡፡
11. ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመሆን ስለተለያዩ የቤተሰብ፣ አገራዊ፣ አካባቢያዊ ጉዳዮች በማንሳት የመወያየት ልማድ ሊያዳብሩ ይገባል፡፡
T.A (MA in Developmental Psychology)
Sources
Heather L. Kirkorian, Ellen A. Wartella, (2008) Media and Young Children’s Learning: 18 / NO. 1 / Retrived in http://
www.futureofchildren.org
Children, Adolescents, and the Media, October 2005 Revised February 2014 by Jane Anderson, MD Revised July 2016 by Jane Anderson, MD
The Impact of Media Use and Screen Time on Children, Adolescents, and Families American College of Pediatricians – November 2016