#ነውርእናወንጀል መጀመሪያ ተመልካች ለመሳብ ያደረጉት ርዕስ መስሎኝ ነበር (በእርግጥ እሱም ቢሆን ሩብ እንኳ ልክነት አይኖረውም ፕሮግራሙ ውስጥ ያለው ድድብና የባሰ ሆኖ ከቨር ስለሚያደርገው እንጂ)
ፍልፍሉ "ይቅርታ ሴት ደፍሬ አውቃለሁ..." ሲል ጃሉድ ቀለል አድርጎ "የምን ይቅርታ ነው? ፈጣሪውንስ ሚዳፈር አለ አይደል እንዴ? ኖርማል ነው" ይለዋል።
ጥላሁን ይቀበልና "አዎ ስንት ነገር አለ አይደል ይሄማ ኖርማል ነው። የእኔን አባት ጨምሮ አብዛኛው ወንድ ጠልፎ'ና ደፍሮ ነው ያገባው" ብሎ ስለ አስገድዶ መድፈር የሰራውን ዘፈን ይዘፍናል።
ደፈራት ደፈራት ደፈራት
መሬት አስተኝቶ እያንፈራፈራት
እኛ እስከምናውቀው ከጥንት ጀምሮ
ሁሉም ሰው ያገባው አስገድዶ ደፍሮ
ከጀርባቸው ብዙ ሳቅ አለ የሚያወሩት እና የምሰማው የተለያየ እስኪመስለኝ ድረስ ።
ምንድነው ልትነግሩን የፈለጋችሁት? ምንድነው የምታደርጉት? ሚዲያውስ ልክነቱን አምኖበት፥ ሀሳቡን ተቀብሎት ነው ፕሮሰሱን ሁሉ አሳልፎ እንዲተላለፍ ያደረገው? አልገባኝም
Via Beza Wit
@EliasMeseret