የተመድ ውሳኔ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው
_የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ህወሓትን ለምን በክፉ ዓይን አየሽብኝ በሚል በኢትዮጵያ የሚሰሩትን ኬንያዊቷን የሥራ ኃላፊ ከሀላፊነት ማንሳቱን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።
አሸባሪውን ድርጅት “ቆሻሻ“ እና “ጨካኝ” በሚል የገለጹትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አለቆችን ለአማጺው ቡድን ይወግናሉ በሚል ያጋለጡት በኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ ሞሪን አቺንግ ከኒውዮርክ በተላለፈ ትዕዛዝ በትላንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ተደርጓል።
ይሄንን ተከትሎም ኬንያዊያንን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ውሳኔውን በመቃወም ላይ ይገኛሉ። ሞሪን አቺንግ ስለትግራይ ሁኔታ ሀሳባቸውን ባጋሩበት የድምፅ ቅጂ ላይ “ህወሓቶች ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመለሱ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ እያሴሩ ነው፤ እና ከዚያ ከሩዋንዳ ምን አይነት የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር አታውቁም። ብቻ ግን ያለው ነገር ቆሻሻ ነው” በማለት ገልፀዋል።
ተመድ 7 የድርጅቱ ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ከአሸባሪው ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ቅሬታ ችላ ብሎ ቡድኑ እያደረሰ የሚገኘውን ጥፋት ብሎም የተመድን ያልተገባ አቋም የተቹትን ኃላፊ ከሥራ ማሰናበቱ የድርጅቱን ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ሆኗል።
የተመድን እርምጃ በመቃወም ድምጻቸውን ካሰሙት መካከል የሆኑ ኬንያዊያን ”በጥቁር አድሏዊነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኬንያዊቷን ሞሪን አቺንግ ለእውነት በመቆማቸው እና ህወሓት በኢትዮጵያ ውስጥ የፈጸማቸውን ጭካኔ በማውገዛቸው ከሥራ አግዷቸዋል። ማስፈራራት ቢኖርም እንኳን ኬንያውያን ሁል ጊዜ ለኢትዮጵያ ይቆማሉ።“ በሚል ገልጸዋል።