ጸሎት ማድረግ የምችል አይመስለኝም።ሁልጊዜ ለጸሎት ስቆምም ሆነ ስንበረከክ የምለው ይጠፋኛል።ምስጋና ሳበዛ የጎደለኝ ትዝ ይለኛል።ጥያቄ ሳበዛ የተደረገልኝ በዐይነ ሕሊናዬ ይመጣና ውለታ ቢስ የሆንኩ ይመስለኛል።ወዲያው ደግሞ ግሳንግስ ኃጢአቴ ትዝ ይለኝና የማመስገንም የመጠየቅም ሐሳቤ ይጠፋና ሀፍረቴ ይመጣል።ለማመጣጠን ስምክር ደግሞ ጸሎቴን ትቼ ስራ የያዝኩ ይመስለኛል።በቃል ያጠናሁትን የተለመደ ጸሎት ባደርግ ይሻላል ብዬ ስጀምር ራሴን መጨረሻው ላይ አገኘዋለሁ።በንባብም ቢሆን ያው ነው።አንዳንዴ ለራሴ፦
"ሰው እንዴት ከፈጣሪው ጋር መነጋገር ያቅተዋል? ከስንቱ የሰው ዓይነት ጋር እየተግባባሁ እንዴት ከአምላኬ ጋር መግባባት ያቅተኛል?" እያልኩ በራሴ አዝናለሁ።
📓ርዕስ፦ሚተራሊዮን
✍️ደራሲ፦አለማየሁ ዋሴ
📚 @Bemnet_Library
"ሰው እንዴት ከፈጣሪው ጋር መነጋገር ያቅተዋል? ከስንቱ የሰው ዓይነት ጋር እየተግባባሁ እንዴት ከአምላኬ ጋር መግባባት ያቅተኛል?" እያልኩ በራሴ አዝናለሁ።
📓ርዕስ፦ሚተራሊዮን
✍️ደራሲ፦አለማየሁ ዋሴ
📚 @Bemnet_Library