"በእምኒ" ስለኦሾ ተናገር ይሉኛል።በጣም ስለተደጋገመብኝ የራሴን ሀሳብ በዚህ መልኩ ሰጥቻለሁ!
አንዳንዶች ሰውዬው እብድ ነው።ሰውዬው ያሳብዳል።መጽሐፎቹ ምንም አይጠቅሙም።ሀሳቦቹ አያንፁም።የሚያናገራቸው ነገሮች በሙሉ ወደ እብደትና ወደለየለት ጥለቻ ይመራሉ ይላሉ።አንዳንዶቹ ደግሞ ሰውዬው እውቀት አለው።ቃላቶቹ የሚጥሙ ናቸው።ከሌሎቹ አሳቢያን በተለየ የራሱን መንገድና አስተምሮት ይዞ የመጣ መምህርና የእውቀቶች ሁሉ አባት ነው ይላሉ።
እኔ ማንንም አላቃወምም።ከማንም ጋር ስለ እሱ ጥሩነት ወይም መጥፎነት በእርግጠኝነት መናገር አልችልም።ግን ኦሾ በእኔ እይታ ሁሉም ሰው ያለውን የሚመስል ሰው ነው።እብድም ነው፤ድንቅም ነው።ቀውጢም ነው።የተረጋጋም ነው።ስለ እሱ መጽሐፎችን አገላበጥኩ።ለራሴ ኦሾ የእውነት ማነው ብዬ ጠየኩ።እናም ብዙ መልሶቹን አገኘው።ኦሾ ጠላቱ ብዙ ነው።ኦሾ ወዳጁም ብዙ ነው።ብቻ ሰውዬው በሁሉም ሰው አይን የተነቀፈውንም የተወደሰውንም አይነት ባህሪ የያዘ ነው።
እስከዛሬ ጥቂት መጽሐፎችን አንብቤያለሁ።ስለ ስሜት፤ስለ እውቀት፤ስለ አካል፤ስለ አዕምሮ፤ስለ ስብዕና፤ስለ ውስጣዊ ስሜት፤ስለ አመለካከት ዘውግ ያላቸውን መጽሐፎች ቀመስመስ አድርጌያለሁ።የተረዳሁት ነገር እንደ ኦሾ አይነት ልዩ የሆኑ መጽሐፎች ጥቂት መሆናቸውን ብቻ ነው።
ሰውዬው አደገኛ ነው።ሰውዬው ጥበበኛ ነው።ሰውዬው ጥልቅ ሀሳቢ ነው።ሰውዬው እብድ ነው።ሰውዬው ብዙ ብዙ ነው።እኔ እብደቱን አውቃለሁ።አስደናቂነቱንም እንደዛው አውቃለው። የኦሾን መጽሐፍ አንብባችሁ እውቀት አለማግኘት አትችሉም።በቃ እሱ ያለውን ነገር ለመስጠት የሚሳሳ አይደለም።ግን እኛ አቀባበላችንን ማስተካከል ይኖርብናል።የእሱን መጽሐፍ ለማንበብ ስናስብ መጀመሪያ ጥሩውን ነገር እንዲጠቅመን ለማድረግ፤መጥፎውን ነገር ደግሞ እንደምንም አለማየት ነው።ትኩረት አለመስጠት ነው።በቃ ትርጉም እንዳይሰጠን ማድረግ ነው።እሱ እኛን ለማሳመን የማያደርገው ጥረት የለም።ግን እኛም እሱን ላለማመን ጥረት ማድረግ አለብን።ከዚህ ውጪ ሌላ ነገር የለም።
✍️ Bemni Alex