~ ~ህብረት
የሀጥያት ጮሮቃ
ባያልኮሰኩሰው
"ሰው " የመሆን ክብሩ
የመንፈስ ልዕልናው
በእግዚአብሔር መልክ ከመፈጠራችን
ከ...ከፍታ ሰገነት
የምንዘግነው ዕሴት...
ሀዘኔታ ፥ ርህራሄ ፥ መስዋዕትነት፥
ከደመ ነፍስ በላይ
ሰው ስለሆንንበት
የሕይወት ክብርና የህላዌ ብርሃን
ነበር.....
የምንቀዳጀው ! ! !
ዛሬ ፥ዛሬ ፥ግን
ሰውነት ፥ተዋርዶ
ስብዕና ፥ ደቆ
አራጅ ፥ለወንድሙ
ካራ ፥ስሎ ፥ቆሞ
ሰው "ሰው "አረደ
እነ እንትና ስፈር
የዲያቢሎስ ፤ሆነ
የአዳም፤ ልጅ፤ ግብር
እግዚኦ ! ይታረቀን!
የሀጥያት ጮሮቃ
ባያልኮሰኩሰው
"ሰው " የመሆን ክብሩ
የመንፈስ ልዕልናው
በእግዚአብሔር መልክ ከመፈጠራችን
ከ...ከፍታ ሰገነት
የምንዘግነው ዕሴት...
ሀዘኔታ ፥ ርህራሄ ፥ መስዋዕትነት፥
ከደመ ነፍስ በላይ
ሰው ስለሆንንበት
የሕይወት ክብርና የህላዌ ብርሃን
ነበር.....
የምንቀዳጀው ! ! !
ዛሬ ፥ዛሬ ፥ግን
ሰውነት ፥ተዋርዶ
ስብዕና ፥ ደቆ
አራጅ ፥ለወንድሙ
ካራ ፥ስሎ ፥ቆሞ
ሰው "ሰው "አረደ
እነ እንትና ስፈር
የዲያቢሎስ ፤ሆነ
የአዳም፤ ልጅ፤ ግብር
እግዚኦ ! ይታረቀን!