ቅርብ ወራጅ! አንዲት እናት በጠዋት ተነስታ ወደ ስራዋ ለመሔድ ትራንስፖርት ትጠብቃለች ነገር ግን ታክሲ ስላላገኘች በባስ ቦታ አግኝታ ትሔዳለች ከአጠገቧ ባዶ ቦታ
ስለ ነበር የሆነች ወጣት ልትቀመጥ ብላ በያዘችው ጥላ ሹል ስለነበር በስለቱ እጇን ትተረትራታለች ከእናትየውም ትንሽ የማይባል ደም ይፈሳል እንደገና ቁጭ ልትል ስትልም ገፈተረቻት ተረጋግታ ተቀምጣ ሳለች ይህች ወጣት ዞር ስትል ከእናትየው ምንም አይነት ቁጣ የተኮሳተረ ፊት አላሳየቻትም ለዚህም ጨንቋት "ለምን አልተቆጡኝም "ለምንስ አይናገሩኝም "ስትል ትጠይቃቸዋለች በዚህ ጊዜ የእዚህች እናት መልስ ልቧን አስደነገጠው...."ቅርብ ወራጅ ነኝ!! "ስትል ትመልስላታች።
ረጅም ጉዞ የምንጓዝ መስሎን በምድር ላይ በማይሆን በሚሆን ስንጨቃጨቅ አንተነህ አንቺ ነሽ ብለን እጅ ስንቀሳሰር በዘር በሀይማኖት ጥምብርቁሳችን ሲወጣ ጥልና ክርክር መለያየት አድማ ገኖ በሁሉ በዝቶ የፍቅር ውሀ ጠምቶት ወንድም ሲመጣ ምላሹ የጥላቻ ውሀ ስናጠጣው ይቅር ማለት መተው ትተን ቂማችንን በጀርባችን ተሸክመን ለመሔድ ለምን ወሰንን? እኮ ለምኔ ይሁሉ? ማቴው ሄነሪ እንዲህ አሉ"እያንዳንዱ ቀን ጉዳያችን ሊሆን የሚገባው ነገር ለመጨረሻ እለታችን መዘጋጀት ነው።"
....ለካ እረስተነው ነው አንጂ ሁላችንም ቅርብ ወራጅ ነን!
" የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤"
-ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5: 9-10
#ትንሽ እንደሚቀረው ፣ብዙ እንደማይሔድ፣በቅርቡ እንደሚቆም፣ እያሰብን በብርሃን እንመላለስ !!!መልዕክቴ ነው
✍ Meron [
@mercy1te]
ተወዳጆች ተባረኩ! 👐
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥
@CHRIST_TUBE ➥
@CHRISTFAMILYሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!