"ዳሸን ባንክ ሴቶችን በሁሉም መስክ ብቁ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ የሚሆን ነው" - ስህን ተፈራ (ዶ/ር) የዘርፉ ባለሙያ
ዳሸን ባንክ የሴት ሠራተኞቹን አቅም ይበልጥ ለማጎልበት የሚያስችል መርሃ-ግብር አስጀመረ። መርሃ-ግብሩ የሴቶችን የመሪነት ሚና ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል።
በመርሃ-ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ “ዛሬ የምንኮራባቸው የአገራችን ታሪካዊ ድሎችን እንድንጎናፀፍ ሴቶች ከፍተኛ አስተዋፅዎ አበርክተዋል” ብለዋል፡፡
በታላላቅ አገራዊና ተቋማዊ ስኬቶች ጀርባ የሴቶች ሚና የጎላ መሆኑን የገለጹት አቶ አስፋው ሴቶች ተገቢው ዕውቅና ሊሰጣቸው አንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ዳሸን ባንክ ይህን ክፍተት በአግባቡ ተገንዝቦ የሚሰራ በመሆኑ ከምስረታው ጀምሮ ሴቶችን በከፍተኛ የአመራር ዕርከኖች ላይ በመሾም ወደፊት በማምጣት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
ዳሸን ባንክ ሴቶችን በአግባቡ ያካተተ አሰራር በመፍጠር አዳዲስ ፈጠራዎችንና ውጤታማነትን እንደሚያጎለብት ተመላክቷል፡፡
መርሃ-ግብሩ ባንኩ ሁሉም ሰራተኞች ዕኩል ዕድል የማግኘትና የማደግ እድል እንዲያገኙ ለማድረግ ካለው ራዕይ ጋር አብሮ የሚሄድ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡
በዳሸን ባንክ የሠው ሐብት ዋና መኮንን ወ/ሮ ህይዎቴ ከፈለኝ በበኩላቸው “ፕሮግራሙ በባንካችን ለወደፊት ከፍተኛ አመራር መሆን የሚችሉ ሴቶችን ከወዲሁ ለመለየትና ለማብቃት የተነደፈ ነው” ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ሐሳባቸውን ያጋሩት የ'ሴታዊት ንቅናቄ' መስራች ስህን ተፈራ (ዶ/ር) ዳሸን ባንክ ሴቶችን በሁሉም መስክ ብቁ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።
በመድረኩ የፓናል ውይይት ተደርጓል።