ዳሸን ባንክ አጋር የሆነበት ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ተከናወነ
ከዳሸን ባንክ አጋር በመሆን የተዘጋጀው የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር በከፍተኛ ድምቀት ተከናወነ፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሚያከናውናቸው ዓመታዊ ውድድሮች መካከል ላለፉት 22 ዓመታት በስኬት የተጓዘው የቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ. ሩጫ ውድድር በብዙ አጋር ተቋማት ድጋፍ ስኬታማ እየሆነ የመጣ ውድድር ሲሆን፣ ዘንድሮ በተካሄደው ውድድር የተሳተፉ ከ16,000 በላይ ተሳታፊዎች የውድድሩ አጋር በሆነው ዳሸን ባንክ ቅርንጫፎችና በሳፋሪኮም ኤም ፔሳ እንደተመዘገቡ ይታወሳል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት በቀረበው “ሁሉም መብቶች ፤ ለሁሉም ሴቶች” በሚል መሪ ቃል በተደረገው ውድድር፣ዳሸን ባንክ በቅርቡ ይፋ ያደረገውንና በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የመጀመሪያ የሆነውን መተግበሪያ (ሱፐር አፕ) አስተዋውቋል፡፡
በተጨማሪም ዳሸን ባንክ ለሩጫው ተሳታፊዎችና ታዳሚዎች በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የከፈተውንና ለደንበኞች በርካታ የተለያዩ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎቶችን መስጠት ያስቻለውን ዳሸን ሱፕር አፕ የማስተዋወቅ ስራ ሰርቷል፡፡
በውድድሩ ላይ በዳሸን ባንክ ስያሜ የተጠራ የአምባሳደሮች ውድድር የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህ ውድድር አሸናፊ ለሆኑት የኦስትሪያ፣ የቤልጅየምና የአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮች የዳሸን ባንክ ቺፍ ፒፕል አፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ህይወቴ ከፈለኝ ልዩ ሽልማቶችን አበርክተዋል።
በተጨማሪም ተምሳሌት ሴቶችን ለማመስገን የተሰየመውን ውድድር ላሸነፉት ተሳታፊዎች የተዘጋጀውን ውድድር የዳሸን ባንክ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ ኤልያስ ሁሴን አበርክተዋል።