እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር
በብዙ መልካም የሆነ ሰውን አንድ ክፉ ነገር ብናይበት ብዙ መልካም ነገሩን ሳይሆን ክፉ ነገሩን አይተን ጉድለት ይሰማናል። አእምሯችን ነጭ ወተት ላይ አንዳረፈ ዝንብ ክፉውን ትኩረት ሰጥቶ ያያል፤ ልባችንም መውደድ ይከብደዋል። ይህ ግን የሥጋ እውቀትና ግብር ነው።
እግዚአብሔር እንደዚህ ቢሆን ኖሮ መወደድ እና መዳን አይገኝም ነበር። በእርሱ ዓይን ብዙ ክፋታችን የተገለጠ ነውና። ነገር ግን እርሱ መልካም ስለሆነ በኃጢአት እየኖርን ጠላቶቹ እያለን ወደደን፤ ያውም እስከ ሞት በሚያደርስ ፍቅር። ለዚህ ቸርነትና ፍቅር አንክሮ ይገባል! (ሮሜ. 5፥10)ይህ አምላካዊ ቸርነት በእኛ ዘንድ ለእምነት፣ ለፍቅር እና ለተስፋ ምንጭ ነው።
እምነት ማለት ሳይገባን ክፉዎች ሆነን የወደደን እና ቀድሶ እና አክብሮ መልካም ልጆቹ ያደርገን ዘንድ ወደ እርሱ የጠራን አምላክ መኖሩን ተረድቶ በእርሱ ታምኖ መኖር ነው። ከዚህም ምሥጋና እና ደስታ ይወጣል። (ዮሐ. 14፥1)
ፍቅር ደግሞ በሥራ እግዚአብሔርን መምሰል ነው፤ እሱ ያለ ጥቅም እና ማዳላት ሁሉን ይወዳልና፤ ጠላቶች ሆነን ሳይቀር ወዶናልና። በእኛ ውስጥ ያለውን ክፋት አይቶ ሳይተወን መልካም አድርጎ መፍጠሩን አስቦ ሊያድነን መጥቷልና።
ተስፋ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ እና ርስትን እየጠበቁ መከራን መታገስ እና የክርስቶስን መምጣት መጠበቅ ነው። እኛን ያድን ዘንድ አንድያ ልጁን ለመከራ አሳልፎ የሰጠ መልካሙ እረኛችን እና አባታችን የማይሰጠን ምን ነገር አለ?የሚጠቅመንን እና ቃል የገባልንን ሁሉ ይሰጠናል። (ሮሜ. 8፥32) ፍቅር ግን ከሁሉም ይበልጣል አለ ሐዋርያው። እውነተኛ ፍቅር ያለው ሰው ሕግን ሁሉ ፈጽሟልና። (1ኛ ቆሮ. 13፥13)
@deaconchernet