"የሀገሬን ህዝብ ለማስደሰት እሰራለሁ" - ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን
**************
የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስደሰት እሰራለሁ ሲል አዲስ የተመረጠው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ተናገረ፡፡
በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፕሬዝዳንትና የሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ተጠናቋል፡፡
የፌዴሬሽኑ አዲሱ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በጉባኤው ላይ ባደረገው ንግግር፤ ፕሬዝዳንት ሆኜ ይህንን ሀገራዊ ኃላፊነት እንድሸከም ስለመረጣችሁኝ አመሰግናለሁ ብሏል፡፡
በአደረጃጀት፣ በሪፎርም፣ በማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራም ገልጿል፡፡
የአበረታች መድሀኒት (ዶፒንግ) ጉዳይ የትኩረት አቅጣጫዬ ነው ያለው ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፤ ዘመናዊ ስልጠናን ተግራዊ እንደሚያደርግም ተናግሯል፡፡
ከ100 ሜትር እስከ ማራቶን ብሎም የሜዳ ላይ ተግባራት ላይ ትኩረት አድረጎ እንደሚሰራም ገልጿል፡፡
በሃብታሙ ካሴ