የህዳሴው ግድብ ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሀብት በአግባቡ መጠቀም እንደምትችል ያረጋገጠ ነው - ምሁራን
**********************
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሀገሪቱ ያላትን የውሃ ሀብት በአግባቡ መጠቀም የሚያስችላትን አቅም መፍጠሯን በተግባር ያረጋገጠ ፕሮጀክት መሆኑን የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ገለጹ።
ምሁራኑ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር ተጋብዘው ከመጡ ምሁራን እና ሳይንትስቶች ጋር ምክክር አድርገዋል።
በምክክሩ ላይ ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሀብቶች በተገቢው መጠቀም የሚያስችል አቅም መገንባቷንና ለዚህም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማሳያ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ምሁራን ገልጸዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት ደረጃም እንደ ሀገር ያሉንን ፀጋዎች ማልማትና መጠቀም የሚያስችል ትምህርት የወሰድንበት ነው ብለዋል።
በምክክሩ የተገኙት በአሜሪካ የቀድሞው የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ፤ ኢትዮጵያ በውሃ ምህንድስናው ያካበተችው ልምድ ከራስ አልፎ ለአፍሪካ በሚጠቅም አግባብ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0JztQRPzsABoTpqeV7fBySVuwGgobbKre3mcqtHssbfVBt4orXbMQqCqB5LafXRLsl