የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈፀመ
***************
የአንጋፋው ፖለቲከኛ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የቀብር ስነ-ስርዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡
የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ አስከሬን ለገ ጣፎ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል።
ከሽኝቱ በኋላ የቀብር ስነ-ስርዓታቸው ቤተሰቦቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ህልፈታቸው እስከተሰማበት ቀን ድረስ ሀገራቸውን በተለያዩ ዘርፎች ያገለገሉና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰላማዊ ትግል ውስጥ ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረከቱ ሰው ናቸው፡፡