በተጠባቂው ጨዋታ አርሰናል ሪያል ማድሪድን 3 ለ 0 አሸነፈ
******
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ኤምሬትስ ላይ የውድድሩን ባለሪከርድ አሸናፊ ሪያል ማድሪድን ያስተናገዱት መድፈኞቹ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
100 ሚሊዮን ፓውንድ ወጥቶበት ሰሜን ለንደን የደረሰው ዴክላን ራይስ ያስቆጠራቸው ሁለት ድንቅ የቅጣት ምት ግቦች እንዲሁም ስፔናዊው አማካኝ ሚኬል ሞሪኖ ያከላት አንድ ግብ የአርሰናልን ድል 3 - 0 እንዲሆን አስችለዋል፡፡
ኪልያን ምባፔ ቪንሺየስ ጁንየርንና ጁድ ቤልንግሀምን የያዘው የማድሪድ ወርቃማ ስብስብ በእንግሊዝ ምድር አስደንጋጭ ሽንፈት አጋጥሞታል፡፡
በሃብተሚካኤል ክፍሉ