✅ለአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የቻይናዉ ዲፕሲክ ስኬት የማንቂያ ደዉል ነዉ ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ
📍የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰው ሰራሽ አስተዉሎት ኢንተለጀንስ (AI) ሞዴል በዎል ስትሪት ግብይት ላይ አስደንጋጭ ስኬት ማግኘቱን ተከትሎየቻይናውን ዲፕሲክ ኩባንያ መነሳት ለአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ “የማንቂያ ጥሪ” ነዉ ብለውታል።እንደ ኒቪዲ ያሉ ዋና ዋና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አክሲዮኖች በከፍተኛ ሁኔታ የተቀዛቀዘ ሲሆን ፣ ግዙፉ ቺፑ 600 ቢሊዮን ዶላር የአክሲዮን ገበያ ዋጋ አጥቷል።
📍ኢንደስትሪውን ያናወጠው የ DeepSeek የ R1 ሞዴሉ ከተቀናቃኞቹ ዋጋ በትንሹ የተሰራ ነው፡፡ ስለወደፊቱ የአሜሪካ ሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት የበላይነት እና የአሜሪካ ኩባንያዎች እያቀዱ ስላሉት ኢንቨስትመንቶች መጠን ጥያቄዎችን አስነስቷል።ዲፕ ሲክ ከጀመረ ከአንድ ሳምንት በኋላ በአሜሪካ ውስጥ በጣም ዳዉንሎድ የተደረገ ነጻ መተግበሪያ ሆኗል።ለዜናው ምላሽ ሲሰጡ ትራምፕ በቻይና ሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ኢንዱስትሪ ውስጥ የተከሰቱት የቅርብ ጊዜ ለውጦች ለአሜሪካ “አዎንታዊ” ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል ።
📍በርካሽ ማድረግ ከቻሉ፣ ባነሰ እና ተመሳሳይ ውጤት ላይ መድረስ ከቻሉ፣ ይህ ለኛ ጥሩ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ ሲሉ ተደምጠዋል።ዩናይትድ ስቴትስ በዘርፉ የበላይ ሆና እንደምትቀጥልም ተናግረው ስለ ግኝቱ ስጋት እንዳልገባቸዉ አክለዋል፡፡ሆኖም ግን ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያዎችን ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርገው የሰሩ ቢሆንም ይህ ጀማሪ የቻይና ኩባንያ ግን በትንሽ ወጪ ተሰርቷል።
📍በቀላሉ ዲፕሲክ ማለት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የጎለበት ቻት ቦት ሲሆን፣ እንደ ቻትጂፒት ያለ ነው።ይህ በ Apple's app store ላይ በብዛት እየወረደ ያለ ነጻ መተግበሪያ ነው፡፡ ዲፕ ሲክ"ጥያቄዎችዎን ለመመለስ" ተብሎ የተዘጋጀ ነው።
══════❁✿❁═══════
🎮▩♦️. @ELA_TECH
🎯▩♦️. @ELA_TECH_GROUP
🚀▩♦️. @ELA_TECHBOT