✅ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የጋራ ተጠቃሚነት አፍሪካዊያንን የሚያሰባስብ ሕብረት ተመሰረተ፡፡
📍አፍሪካ ኤ.አይ ካዉንስል የተሰኘዉ ሕብረቱ አህጉሪቱን በዘርፉ በዓለማቀፍ ደረጃ ቁልፍ ተዋናይ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡ በዚህም አፍሪካ ከቴክኖሎጂው ተጠቃሚነት ባሻገር ለዘርፉ እድገት ዓለማቀፍ አበርክቶ እንዲኖራት ያስችላል፡፡ ሕብረቱ መንግሥታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ አፍሪካዊያን የዘርፉ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎችን ያካተተ መሆኑን ቴክ አፍሪካ ድረ-ገጽ ዘግቧል፡፡
📍አፍሪካ ኤ.አይ ካዉንስል የበርካታ ወጣቶች መገኛ የሆነችዉ አፍሪካ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስክ ያላትን የሰዉ ኃይል አቅም ለማሳደግ በትብብር መስራት የሚያስችላትን እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡
📍ለሕብረቱ መመስረት ምክንያት የሆነው ስማርት አፍሪካ ኢንሼቲቭ የተባለው ተቋም ዋና ስራ አስፈጻሚ ላሲና ኮኔ የሕብረቱ ምስረታ ሥነ-ምግባራዊ የሆነ የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ አፍሪካን በዘርፉ ዋና ተዋናይ እንድትሆን ያስችላታል ብለዋል፡፡
📍የአፍሪካ ኤ.አይ ካዉንስል 15 የቦርድ አባላት ያሉት ሲሆን ግሎባል ኤ.አይ ሰሚት በተባለው ሁነት ላይ በይፋ ይመሰረታል፡፡ ግሎባል ኤ.አይ ሰሚት በፈረንጆቹ ኤፕሪል 3 እና 4፤ 2025 በሩዋንዳ የሚዘጋጅ ጉባኤ ነው፡፡
📍ስማርት አፍሪካ ኢንሼቲቭ በአፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማሳካት በ7 የአፍሪካ ሀገራት መስራችነት የተመሰረተ ነዉ፡፡ ኢንሼቲቩ 40 አጠቃላይ አባል ሀገራት እና በርካታ አጋር አካላት አሉት፡፡
══════❁✿❁═══════