✅ ኦፕን ኤ.አይ GPT-4.5 እና GPT-5 የተባሉ አዳዲስ የኤ.አይ ሞዴሎችን ይፋ ሊያደርግ ነው፡፡
▪️የኦፕን ኤ.አይ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን GPT-4.5 እና GPT-5 ስለተባሉ ሞዴሎች በኤክስ የማሕበራዊ ትስስር ገጹ መረጃ አጋርቷል፡፡ መረጃው ኩባንያው ሁሉንም የኤ.አይ ሞዴሎች ወደ አንድ የተዋሀደ ሥርዓት ለማምጣት እየሰራ እንደሚገኝ የሚገልጽ ነው፡፡
▪️እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው መረጃ ከሆነ GPT-4.5 ወይም ኦሪዮን ተብሎ የሚጠራው ሞዴል ለሚያቀርባቸው ምላሾች ምክንያታዊነትን የማያካትት የኩባንያው የመጨረሻ ሞዴል እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡ ይህም ከዚህ በኋላ በኦፕን ኤ.አይ ይፋ የሚሆኑ ሞዴሎች የሚያቀርቡት ምላሽ ምክንያትን ያካተት እና ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ የማሰላሰል ሂደት የሚከተሉ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
▪️ከእነዚህ ሞዴሎች ይፋ መሆን በኋላ የኩባንያው ዋና ግብ ኦ-3 ተብለው የሚታወቁትን ሞዴሎች እና የጂ.ፒ.ቲ ተከታታይ ሞዴሎችን አንድ ማድረግ ነው። በውጤቱም ኦ-3ን ጨምሮ ሌሎቹንም የሚያጠቃልል GPT-5 እንደሚለቀቅና የኦ-3 ሞዴል ከዚህ በኋላ ራሱን የቻለ ነጠላ ሞዴል ሆኖ እንደማይቀጥል ታውቋል።
▪️GPT-5 የተለያዩ ሞዴሎች አሁን ላይ የሚከውኑትን ተግባራት በአንድ የሚያጠቃልል ማዕከላዊ ሞዴል ከመሆን በሻገር በከፍተኛ የአስተውሎት ደረጃ ስራዎችን የሚከውን እንደሚሆን የዋና ስራ አስፈጻሚው መረጃ ያመላክታል፡፡
▪️አልትማን ሞዴሎቹ የሚለቀቁበትን ቀን በግልፅ ባያስቀመጥም በሳምንታት አልያም በጥቂት ወራት ውስጥ ለተጠቃሚዎች ይፋ እንደሚሆን ታውቋል፡፡
══════❁✿❁═══════