▪️|| ህልም ሰራቂዉ ጉዳት !
- በእግርኳስ ዉስጥ እጅግ በጣም ደባሪዉ ነገር ጉዳት ነዉ ። ጉዳት የብዙዎችን ህልም ፣ የብዙዎችን ብቃት ፣ ተስፋ ፣ ተሰጥዖ ቀምቷል ። የት ይደርሳሉ የተባሉ ጉዳት ሰርቋቸዋል ። ከመስርቅ አልፎ አስርስቷቸዋል ። በዚህ ከተጠቁ ተጫዋቾች መሀል ኬራን ቲርኒ አንዱ ነዉ ። በክፉ ጊዜ የነበረ ድንቅ ተጫዋች ፤ ሙሉ ቡድኑ በሚፈዝበት ሰአት ደሙን አንጠፍጥፎ የሚሰጥ ደመኛ ። የ አምበልነት አርማዉን ያላጠለቀ የቡድን መሪ ፣ ኮስታራ ለመፋለም የተዘጋጀ ልባም ነበር ። በብዙዎቻችን የሚወደድ አንድ ወቅት ተስፋ የጣለበት ፤ የወደፊቱ አሽሊ ኮል ተብሎ ሰም የወጣለት ተጫዋች ጉዳት እንዳልነበረ አርጎ አስርስቶት ብዙ ዕድሜ ቀንሶበታል ።
- ጉዳት እንደምናስበዉ ቀላል አይደለም ። ምንአልባት የ ኔይማርን documentary film ብታዩት እና ጉዳት ልጁን ለማቀፍ ራሱ እንደገደበዉ ብታዩ ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆነ ትረዳላቹ ። ለዚህ ነዉ የ አርሰናል ደጋፊ በ ሮድሪ ጉዳት ሲስቅ ሲቀልድ ሳይ ጤንነቱ የሚያጠራጥረኝ ። ዛሬ እንኳን እኛ ምን ያህል እንደታመስን እዩ ። ነገ የእኛ ተጫዋች ላይ አለመድረሱ ዋስትና የለንም ። ከዚህ ቀደመም እንደ ዊልሸር ፣ ካዞርላ ፣ ራምሴይ ሌሎችንም ኮከቦች ቀምቶናል ። እግርኳስ አንድ አንድ ጊዜ ዕድል አላት ። ለ ኬራን ቲርኒ ዳግም የመጫወት ዕድል ሰጥታዋለች ። እንደምታዉቁት ጉዳት ፈፅሞ አይለቅም ። ተደጋግሞ አንዴ የተጎዳ ተጫዋቾ ላይ ይከሰታል ። ግን ምንአልባት ጥቂት ደቂቃዎችም ቢሆን ከ አርሰናል እስኪወጣ ዳግም መለያዉን ቢያጠልቅ ምኞቴ ነዉ ። ከ አርሰናልም ሲወጣም ቢሳካለት ደስ ይለኛል ።
• ስኮቲሹ ኬቲ ዳግም ሜዳ ላይ ብናየዉ 🙏❤️
"SHARE" . @ETHIO_ARSENAL