እንግሊዝኛ ምን በአለም ቢነገር፣ ምን ቢሊዮኖች ቢመኙት .. እዚያው ከቻይና ብር ይበደሩበት እንጂ፤ ፊልም ይስሩበት እንጂ፤ እንደ እኔ ላለው መች እንደ አማርኛ የልብ ያደርሳል?
✔️እስቲ አሁን "አይዞህ"ን በእንግሊዝኛ ልበልህ ብለው እንዴት ይገለጻል?
እንግሊዘኛ እንደ ቋንቋ መተሳሰብን መች ይደግፋል? እስቲ አሁን እንግሊዝኛ "እኔን እኔን" ብሎ ነገር የት አባቱ ያውቃል? እሱን ተውት "የት አባቱ!" ማለትንስ የት አባቱ አውቆት? ሰው እንቅፋት ሲመታው "እኔን" በሚለው መተሳሰብ ፋንታ "ዋች አውት! አር ዩ ኦኬ? የት ያደርሳል? "ዋች አውት" አጠጋግተን ስንተረጉመው "ምን አባሽ ያደናብርሻል?" አይደለምን?
ጋሽ ስብሃት ገ/እግዚያብሄር - በአንድ ወቅት ከተናገረው የተወሰደ