True story💙
ሀያቴን እንደምወዳት ማንንም ሰው ወድጄ አላውቅም....እንደ እሷ የሚወደኝም ሰው ገጥሞኝ አያውቅም....አጠገቤ ነበር የሞተችው....እንደ ነገ ልትቆርብ ልብስ ተገዝቶላት ገላዋን ታጥባ ነበር የተኛችው....መልሳ አልነቃችም እንጂ....ከሞት ጋር የተዋወቅነው ያኔ ነው....
እሷ ከሞተች በኃላ ከገዛ እናቴ ጋር እራሱ መግባባት አቅቶኝ ነበር....ከቤተሰቦቼ ጋር እኖር ነበር እንጂ ሀያቴን ብቻ ነበር የማውቃት...
የሀያት ልጅ መሆን አንዳንዴ መጥፎ ነው...እሷ ከሞተች በኃላ ነው ጎንበስ ብዬ እጅ ማስታጠብ እንኳን የጀመርኩት....
ያኔ ነገሮች ብዙ አይገቡኝም ነበር....አፈር ስትገባ እኔና ከእኔ በእድሜ የሚያንሰው የአጎቴ ልጅ የሰዉን አለቃቀስ እያየን እንስቅ ነበር....አይገርምም እኔም እሱም ቆይቶ ነው የገባን....ይሄንን አጋጣሚ ስናስታውስ "እነሱ እኮ ያን ቀን እርማቸውን አወጡ....በእኛ ባሰ" ይለኛል...እሱም እናቱን "እንደ እምዬ አይነት ሽሮ ካልሰራሽልኝ አልበላም"....ሲል እራሱን አገኘው....እኔም እናቴን "እምዬ ስለሞተች ነው ምትጫወቺብኝ...."....ስላት አገኘሁት....
"እምዬን አምጣልኝ" ብዬ የፀለይኩትን ሳስብ ወይ ልጅነት እላለሁ....ከሩቅ ነጠላ የለበሱ አሮጊቶችን ሳይ ፊታቸውን እስካጣራ የምሮጠውን ሩጫ አስታውሳለሁ....በውን አልመጣ ስትለኝ በህልሜ እንዳያት ለቀናት በጊዜ ተኝቻለሁ....አላየኃትም።
ሁሉም እሷን ፍለጋ ላይ እንደነበር የገባኝ ቆይቶ ነው....ለካ ይቺ ሴት የእኔ ብቻ ሳይሆን የቤተሰባችን ልብ ነበረች....
ያኔ እናቴን ተቀይሜያት ነበር.....ከሁለት ወር በፊት በሩቅ የምታውቃቸው ሴትዮ ሞተው "እንደው በሄድኩና ባለቀስኩ...የእምዬ አልወጣልኝም..."...ስትል ቅያሜዬን ተውኩት እንጂ...ለካ እሷም እናቷን ነው ያጣችው....
አጎቴ በጥፊ መቶኝ ሲያነስረኝ "እሷ ብትኖር ቀና ብለህ አታየኝም አጎደለችብኝ"...ስለው "መጉደል አይደለም...ባዶ ነው የሆንኩት...."....ብሎ እንደ ሴት ፊቴ ሲያለቅስ ደንግጫለሁ....ለካ እሱም እናቱን ነው ያጣው....ያኔ ከእኔ ውጪ ማንም እንደጎደለበት አላስብም ነበር....ምን አለፋችሁ ትልቅ ሰው የሚያመው አይመስለኝም ነበር....
ሀያቴ ከመሞቷ በፊት ይህ አጎቴ ለአምስት አመት የታቀደ ፊልድ ወጥቶ በአራተኛ አመቱ መተት ተሰርቶበት ፀበል ይገባል...ፀበል ሲሄድ ሸኝተን እንመሳለን ብለን ከወጣነው ቤተሰቦቹ ልጄን ጥዬ አልመለስም አስታምመዋለሁ ብላ የቀረችው እናቱ ነበረች....የእኔ ሀያት....
እንደወጣች ቀረች....አብረው ከሄዱበት ፀበል እሱ ብቻውን ተመለሰ....እናቴ "ሞቱን ወሰደችለት" ትላለች....አንዳንዶች ደግሞ "እናቱ ለእሱ ብላ ወጥታ ቀረች....ሞቱን ሰጣት" ይላሉ.....ሲመስለኝ ሰጣት እና ወሰደችለት መሀል ትልቅ ልዩነት አለ....ሞትን ሰዎች የሚቀባበሉት አንተ ትብስ አንተ ትብስ የሚባባሉት ነገር ባይሆንም "ወሰደችለት" ላይ ፍቅርና ፈቃደኝነት አለ....
ወጣትነት ጥሩም መጥፎም ነው...ego የሚባለው ነገር የሚበረታብን....ገላመጠን ብለን እጃችን ለጡጫ የሚዘጋጅብን....ትዕግስት የማያውቀን....ነገ ምን ይመጣብኛል ብለን የማንጨነቅበት ችግራችንን ለመፍታት ወጣትነታችን ብቻ በቂ እንደሆነ የምናስብበት ጊዜም ነው....
እንደ እኔ እንደ እኔ አጎቴ ወጣትነቱን እየኖረ ነበር..."እሱ እንዲህ ባያደርጋቸው ኖሮ ወይ እንዲያ ቢያደርግ ኖሮ ህይወቱን አያበላሹትም ነበር" ከሚሉት ወገን አይደለሁም....በቃ ለምንም ጥፋት ይሄ ቅጣት አይገባም....ወጣትነት ለጥፋቶች ለአለመግባባቶች የምንሰጠው ጤነኛ ምላሽ ባንኖረን እንኳን በሰላም move ማድረግን ሊያላብሰን ይገባል....ወጣትነታችንን በብልሀት እንኑር....አንድ ሰው ለመጉዳት ስናስብ ከጀርባው ስንት ሰው እንዳለ እናስብ....
ያልተመቸንን ሰው እንተወው.......ያስቀየመንን ሰው ፊት ለፊቱ እንናገረው.... የሰደበንን ልቦና ይስጥህ ብለን ማለፍ ካቃተን ፊት ለፊቱ መልሰን እንስደበው.....እንደ ፈሪ ከኃላ አንተብትብበት....በሰላም ዘወር ብለን የራሳችንን እንኑር....
✍Shewit
https://t.me/shewitdorka