ኅዳር 12 ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡ (እንኳን አደረሳችሁ)
በዓለ ሢመቱ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ በእለተ እሁድ ካለመኖር ወደ መኖር የመጣ ሲሆን እርሱም የነገደ ኃይላት አለቃቸው ነው በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የአጋእዝትን ነገድም በአለቅነት ደርቦ የያዘ ሲኾን፡፡ ለ100ውም(99ኙም) ነገደ መላእክት አለቃቸውም ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (በዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ 13 (የአእላድ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ምሕረትን የሚለምንበት ነው፡፡
በዚህ ቀን የሚከበረው እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እያመራቸው ማውጣቱን ለማዘከር ነው፡፡
ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ በ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ በ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ ፈርኦን በግብፅ ነገሠ፡፡ እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ 430 ዘመን በባርነት ከቆዩ በኋላ ከእብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ እንዲያሳርፉዋት ጠየቀች ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ አሉዋት፡፡ ከመሐጸኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፡፡ ራሔልም አለቀሰች ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባ የሕዝበ እስራኤል ሁሉ ጩኸት እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) በማድርግ ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡
ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ንሴብሆ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ ጠላታቸውን የመታላቸውን እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቢ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው መና ከሰማይ እያወረደላቸው ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ቀኑን በደመና ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጉዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓን ገብተዋል፡፡ /ዘጸ 15/
ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ኢያሱን አነጋግሮታል፡፡
ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቢ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ በረከት ይክፈለን፡፡
#በአዲስ_አበባ_የሚከብርባቸው_ #፵፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (በኦሪት ዘመን መሥዋዕተ ኦሪት ይሰዋበት የነበረ፥ ዋሻ ቤተ ክርስቲያኑ በ4ኛው ክ/ዘመን በአብሃ ወአጽብሃ ዘመን የተመሠረተ)
አድራሻው፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ሾላ መገናኛ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(4 ኪሎ) → ሾላ መገናኛ፤
፪. አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (ራስ ካሳ ሚካኤል) (ጭቁኑ)፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ራስ ካሳ
ታክሲ፤ ከ4ኪሎ(ከ6 ኪሎ) → ፈረንሳይ፡፡
፫. ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (አዲሱ ሚካኤል)
አድራሻ፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፥ አውቶቡስ ተራ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(4ኪሎ) → አውቶቡስ ተራ፡፡
፬. አፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (ወህኒ ቤት) (ከርቸሌ)
አድራሻ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፥ ቡልጋርያ (ከርቸሌ) (አፍሪካ ኅብረት)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ቄራ፡፡
፭. ኮተቤ (ሲኤምሲ) ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ /ሳጠራው/ (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲኤምሲ)
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ካራ አሎ ፥ አባዶ አጠገብ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ሲኤምሲ፡፡
፮. መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ መካኒሳ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → መካኒሳ፡፡
፯. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ላፍቶ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡
፰. ቤተል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ቤተል፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኃሎች → አየር ጤና፡፡
ወይም፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት → አለም ባንክ/ኤር ጤና/፡፡
፱. ኤረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤልና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ጎሮ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ (ፒያሳ) → ጎሮ፡፡
፲. መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅድስት አርሴማ ገዳም፤
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ቀጨኔ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከመርካቶ)(ከአዲሱ ገበያ) → ቀጨኔ፡፡
፲፩. አያት ጨፌ ኢያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ (በ1980ዓ.ም ጽላቱ ከነ ድርሳናቱ ተቀብሮ የተገኘበት)
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 9፥ ጎሮ ሰፈር፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ጎሮ፡፡
፲፪. ካራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤል፥ 24ቱ ካህናተ ሰማይና ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አባዶ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → አባዶ
፲፫. ቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ቦሌ ሚካኤል፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቦሌ ሚካኤል፡፡
፲፬. የካ አባዶ ገ/አ/ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አባዶ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → አባዶ
፲፭. ምሥራቀ ፀሐይ ዳንሴ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤