ጥር_7_በዓለ_ሥላሴ_የሰናዖርን_ግንብ_ያፈራረሱበትና_ቋንቋ_የደባለቁበት_ዕለት፡፡
✤✤✤✤✤
“#ንዑ_ንረድ_ወንዝርዎ_ ከመ_ኢይሳምዑ_ነገሮሙ_አሐዱ_ምስለ_ካልኡ፤›› “ኑ ፥እንውረድ ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማ ቋንቋቸውን እንደባልቅባችው”ዘፍ 11፥7
#በባቢሎን የነበሩት በሰናዖር ሰፊ ሜዳ አግኝተው ‹ሳንሞት ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ› አገር እናቅና እስከ ሰማይ የመሚደርስ ግንብ እንስራ ተባባሉ ፤ማይ አይኀ በወረደ ጊዜ እንዳያጠፋን የምንጠጋበት ግንብ እንስራ ብለው ሥራ ጀመሩ ፤ አንድም ሞትን የሚያመጡብን ሥላሴ ናቸውና እርሱን ገለን ሞትንም እናጠፋለን ሲሉ፡፡
✤ይህንን ግንብ #43 ዓመት ሰርተውታል ቁመቱም #5433 ከ2 ስንዝር ነው፤ በፀሐይም እያበሰሉ ይበሉ ጀምረው ነበር ፡፡
✤ከዚያም ሆነው ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር ሰይጣን ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል እነርሱም ደሙን እያዩ ‹‹ አሁን አብን ወጋነው አሁን ወልድን ወጋነው ….›› ይሉ ጀመር
እግዚአብሔርም የሰናዖርን ግንብ ይጥልባችው ዝንድ ‹‹ንዑ ንረድ ወንዝርዎ ✤ ከመ ኢይሳምዑ ነገሮሙ አሐዱ ምስለ ካልኡ፤›› አሉ የአንዱን ቋንቋ አንዱ እንዳይሰማው ወርደን ቋንቋቸውን እንለያየው ፡፡ ሥላሴ ፍጥረት ሁሉ ቢጎዳ አይወዱምና #72_ቋንቋ አመጡባቸው፤ አንዱ እሣት አምጣ ሲለው አንዱ ውሃ ያመጣል አንዱ ጭቃ ሲል ደግም እንጨት ያመጣለታል፡፡
✤ከዚያም ትተው ወረዱ ነገር ግን ግንቡን እንደ ጣዖት አርገው ማምልክ ሲጀምሩ ሥላሴ ጽኑ ነፋስ አስነስተው በትነውታል፡፡ #ምሥጢረ_ሥላሴን ሲያስረዳ ( “እግዚአብሔርም አለ” አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ድግሞም ኑ እንውረድ አለ ፤ ሶስትነታቸውን ሲያጠይቅ፤) (ዘፍ 11)
#ባቢሎን ማለት ዝርው (ዝሩት) ሲሆነ ቋንቋ እና በቦታ ስለተለያዩበት ስያሜውን አግኝቷል (እግዚአብሔር ቋንቋን በትኗልና፣ አህዛብንም በዓለም ሁሉ በትኗልና፡፡
‹‹…ሥላሴ ሕጸበኒ ወአንጽሐኒ እምአበሳየ በሐሊበ ምሕረትከ ›› ሰይፈ ሥላሴ ዘዓርብ
@Nigatu5