በቻይና የቤት ስራ ባለመስራቱ ቁጣ የደረሰበት ታዳጊ ወላጅ አባቱ አደንዛዥ እፅ እንደሚጠቀም ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠቱ አባት በቁጥጥር ስር ዋሉ
የቤት ስራውን ባለማጠናቀቁ በአባቱ የተገሰጸው የ10 አመቱ ልጅ ፖሊስ በመጥራት አባቱ አደንዣዥ እፅ እንደሚወስድ በመናገር ወላጁን ተበቅሏል።አስገራሚው ክስተት ያጋጠመው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በቻይና ዮንግኒንግ ግዛት ውስጥ ነበር። የ10 አመቱ ታዳጊ የቤት ስራውን በሰዓቱ ስላልጨረሰ በአባቱ ከፍተኛ ተግሳፅ ከደረሰበት በኋላ ከቤት ወጥቶ በቀጥታ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሱቅ ሄዶ ስልክ በመጠቀም ሪፖርት አድርጓል።
የአምስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ታዳጊው 110 ወደ ቻይና የድንገተኛ አደጋ ስልክ በመደወል አባቱ ህገወጥ ዕፅ በቤት ውስጥ እንደሚጠቀም የሚያሳይ ማስረጃ አለኝ በማለት ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥቷል። ከዚያም ፖሊስ እስኪመጣ ተረጋግቶ በመጠበቅ ፍተሻ እንዲያካሂዱ እና የሰጠውን መረጃ እንዲያረጋግጡ አድርጓል። በፍለጋው ወቅት ፖሊሶች በልጁ ቤት በረንዳ ላይ ስምንት የደረቁ የአደንዣዥ እፅ አበባ እንዳገኙና የልጁ አባት መግዛቱን አምኗል።
ነገርግን ለመድኃኒትነት አገልግሎት ብቻ ሊጠቀምባቸው እንዳቀደም አክሏል። የተገኘበት እፅ እንደ አደገኛ እፅ የሚመድበ በመሆኑ ህግ በመጣሱ መፀፀቱን ገልጿል፣ነገር ግን ሳያውቅ ይህን እንዳደረገ አጥብቆ ተናግሯል። ፖሊስ ማስረጃዎቹን እና ተጠርጣሪውን በአቅራቢያው ወደሚገኝ ጣቢያ በመውሰድ ጉዳዩን ለፀረ አደንዛዥ እፅ ብርጌድ አስተላልፏል።የቻይና ፖሊስ ያልተለመደ እፅ በመጠቀም ያለፈቃድ ማምረት ወይም መያዝ ህገወጥ መሆኑን እና አጥፊዎች የወንጀል ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቋል።
ምንም እንኳን የእፁ የደረቁ ቅርፊቶች ለመድኃኒትነት ወይም ህመም ማስታገሻነት ይወሰዳሉ። ለእንቅልፍ ማጣት እና ጭንቀት ለመቀነስ ተመራጭ ነው። ግን ቻይናን ኦፒየም የተባለውን መድሀኒት ከማምረት ጋር የተያያዘ በመሆኑ እፁን ማምረት ህገወጥ ብላ ፈርጃዋለች።
በስምኦን ደረጄ
@Ethionews433 @Ethionews433