✅ቫለንታይን ዴይ' ምንድን ነው? እንዴትስ መከበር ጀመረ?
⭐ይህ ቀን ስያሜውን ያገኘው ከታዋቂው ቅዱስ ቫለንታይን ቢሆንም ስለዚህ ሰው ምንነት ግን የተለያዩ ታሪኮች ይነገራሉ።
✅በርካቶች በሚስማሙበት ታሪክ ቅዱስ ቫለንታይን ሮማ ውስጥ በሶስተኛው ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረ ቄስ እንደሆነ ነው።
✅ይህ ሰው ታዲያ በክርስቲያናዊ መንገድ የሚፈጸም ትዳርን በእጅጉ የሚያበረታታ ነበር።
✅ በወቅቱ የነበረው ንጉስ ክላውዲየስ ትዳር የመሰረቱ ወታደሮች ደካማ ናቸው ብሎ ያምን ስለነበረ ሚስት ማግባት ከለከለ። ቅዱስ ቫለንታይን ታዲያ በዚህ ውሳኔ በእጅጉ ያዝናል፤ ተገቢም አይደለም ብሎ የሆነ ነገር ለማድረግ ተነሳ።
✅ በዚህም የንጉሱ ወታደሮች ሳያዩና ሳይሰሙ ጥንዶችን በሚስጥር ማጋባት ጀመረ። ነገር ግን ይህ ሚስጥር ለረጅም ጊዜ አልቆየም።
✅ንጉሱ ይህንን ዜና በሰማ ጊዜ ቅዱስ ቫለንታይን እስር ቤት እንዲወረወር ትእዛዝ ያስተላልፋል። በኋላም ቅዱስ ቫለንታይን የሞት ፍርድ ተላለፈበት።
በእስር ላይ ሳለም ከእስር ቤቱ ጠባቂ ሴት ልጅ ጋር ክንፍ ባለ ፍቅር ይያዛል።
✅እናም ጥር 14 ላይ በንጉሱ ትእዛዝ መሰረት ሊገደልል በሚወሰድበት ዕለት ለፍቅረኛው ልብ የሚነካ የፍቅር ደብዳቤ ይጽፍላታል። በደብዳቤው መጨረሻ ላይም ያንቺው ቫለንታይን የሚል ጽሁፍ አስፍሮ ነበር።
✅ይህንን ታሪክ የሰሙ የአገሬው ሰዎች ታዲያ ለሚያፈቅሯቸው ወዳጆቻቸው የፍቅር ደብዳቤ ሲጽፉ ግርጌ ላይ ያንቺው ቫለንታይን ብለው መጻፍ ጀመሩ።
ትንሽ ቆይቶም ቅዱስ ቫለንታይን የተገደለበትን ቀን የፍቅረኛማቾች ቀን አድርጎ ማክበር እንደተጀመረ በርካቶች ይገልጻሉ።
✅ነገር ግን ለዚህ ቀን መከበር ምክንያት ናቸው ተብለው የሚጠቀሱ ሌሎች ክስተቶችም አሉ። አንደኛው በዚህ ዕለት የጥንት ሮማውያን በየዓመቱ የሚያከብሩት አንድ በዓል አለ። በዚህ በዓል ወቅት በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች የፍቅር አጋራቸውን የሚመርጡበት ነው።
✅ታዲያ የሮም ቤተክርስቲያን ይህንን በዓል ቤተክርስቲያን ስርዓት ለማድረግ በማሰብ ከቅዱስ ቫለንታይን ታሪክ ጋር በማያያዝ ዓመታዊ በዓል እንዲሆን ስለመደረጉ የሚናገሩም በርካቶች ናቸው።
ቫለንታይን ዴይ ወይንም የቅዱስ ቫለንታይን በመባል የሚታወቀው የፍቅረኞች ቀን በየዓመቱ ተከብሮ የሚውለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር የካቲት (ፌብሪዋሪ) 14 ላይ ነው።
✅በዕለቱ ሰዎች ለፍቅር አጋሮቻቸው ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት ይገልጻሉ። የፍቅር መግለጫ ካርዶች፣ አበባዎች፣ ቸኮሌት አልያም የፍቅር መልዕክት መለዋወጥ የተለመደ ነው።
ምንጭ BBC
@Ethionews433