በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አማፂው ቡድን ኤም 23 ሁለተኛውን ግዙፍ ከተማ ተቆጣጠረ
በሩዋንዳ የሚደገፉት ኤም 23 አማፂያን በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ወደሆነችው ቡካቩ ገብተዋል። በአካባቢው ታጣቂው ቡድን ፈጣን የጦር እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የደቡብ ኪቩ ግዛት አስተዳዳሪ ዣን ዣክ ፑሩሲ ተናግረዋል ። ፑሩሲ እሁድ እለት ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት "የኤም 23 ታጣቂዎች በቡካቩ ውስጥ ይገኛሉ፣የኮንጎ ወታደሮች የከተማ ውጊያ እንዳይደረግ በማለት አካባቢውን ለቅቀው ወጥተዋል" ብለዋል።
የታጠቀው ቡድን በጥር ወር መገባደጃ ላይ የክልሉን ትልቁን ከተማ ጎማ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ ወደ ሌሎች ከተሞች እየገሰገሰ ይገኛል። የቡካቩ በኤም 23 ቁጥጥር ስር መግባት በጣም አስፈላጊ የሆነውን የግዛት መስፋፋት የሚያሳይ ሲሆን ይህም አመፂ ቡድኑ ብረት ካነሳበት ከ2022 ወዲህ የቡድኑ ትልቅ ስኬት ሆኗል። የኮንጐ መንግስት አማፂያኑ ቡካቩ መግባታቸውን አረጋግጦ የሩዋንዳ ወታደሮችም አብረዋቸው ይገኛሉ ብሏል። መንግስት ግን ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በኤም 23 ቁጥጥር ስር መሆኗን አልተናገረም።
ሩዋንዳ በኮንጎ ምድር ላይ ወረራ በማድረግ ለመዝረፍ እና ወንጀሎችን እንዲሁም ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመፈጸም እቅዷን በግትርነት እየተከተለች ትገኛለች ሲል የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል። እሁድ እለት ቀደም ብሎ አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ፣የደህንነት ምንጭ እና አምስት ምስክሮች አማፅያኑን በከተማይቱ ውስጥ ማየታቸውን ሪፖርት አድርገዋል። የታጠቀው ቡድን ቃል አቀባይ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ከተማይቱን መያዛቸውን በማረጋገጥ “እዚያ ነን” ብለዋል ።
በስምኦን ደረጄ
@Ethionews433 @Ethionews433