ለቻይና ድርጅቶች መረጃ አሳልፎ በመስጠት የተጠረጠረው ዲፕሲክ
የደቡብ ኮርያው የግል መረጃ ጠባቂ ኮሚሽን የቻይናውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ድርጅት ዲፕሲክን የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ አሳልፎ እየሰጠ ነው ሲል ወንጅሎታል።
መረጃውንም ለቻይናው ለቲክቶክ እናት ኩባንያ ባይትዳንስ አሳልፎ እንደሰጠ ገልጿል።
ዲፕሲክ ከባይትዳንስ ጋር ግንኙነት መፍጠሩን ደርሼበታለሁ ያለው የደቡብ ኮርያው የግል መረጃ ጠባቂ ኮሚሽን በትክክል ምን ዓይነት እና ምን ያህል መረጃዎች እንደተጋሩ ግን አልገለጸም።
ደቡብ ኮርያ ዲፕሲክን ያገደች ሲሆን ምክንያቷም ከግል መረጃ ደህንነት ጋር በተያያዘ መሆኑን አስታውቃለች።
አውስትራሊያ እና ታይዋንም ዲፕሲክን በመንግስት ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ላይ መጠቀም የከለከሉ ሀገራት ሆነዋል።
አንድ የአሜሪካ የሳይበር ደህንነት ድርጅትም ዲፕሲክ ከባይትዳንስ ጋር ቀጥተኛ የሲስተም ግንኙነት እንዳለው ማስረጃ ማግኘቱን አስታውቋል። በዚህም ዲፕሲክ ለባይትዳንስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የቻይና ድርጅቶች ጭምር መረጃ አሳልፎ ሳይሰጥ እንደማይቀር ጠቁሟል።
ዲፕሲክ ይፋ በተደረገበት የጥር ወር ላይ በርካታ ተጠቃሚዎች ያገኘ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ገበያውን ያነቃነቀ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ነው።
በደቡብ ኮርያ ከመታገዱ በፊት ከአንድ ሚሊየን ጊዜ በላይ ሰዎች ያወረዱት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ነበር።