ናይሮቢ-ጎማ ከተማ ዉስጥ በተደረገ ዉጊያ ከ5000 በላይ ሰላማዊ ሰዉ ተገድሏል-መንግስት
የምሥራቃዊ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ትልቅ ከተማ ጎማ ዉስጥ በተደረገ ዉጊያ በትንሹ 5000 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉን የሐገሪቱ መንግሥት አስታወቀ።የጎማ ከተማን ላለማስያዝና ለመያዝ የኮንጎ መንግስት ጦር፣የአፍሪቃ መንግስታት፣የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወታደሮችና በሩዋንዳ የሚደገፈዉ የM23 አማፂያን ባለፉት ሳምንታት ከፍተኛ ዉጊያ ሲያደርጉ ነበር።የኪንሻ መንግሥት የሩዋንዳ ወታደሮች ከአማፂዉ ቡድን ጋር አብረዉ ተካፍለዉበታል ባለዉ ዉጊያ በትንሹ 5000 ሰዎች መገደላቸዉን ትናንት ማታ አስታዉቋል።የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መንግሥት ቃል አቀባይ ፓትሪክ ሙያያ እንዳሉት እስከ ትናንት ድረስ 5000 ሰዎች መቀበራቸዉን መንግስታቸዉ ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጧል።ይሁንና የሐገሪቱ የጤና ሚንስቴር የሆስፒታል ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የሟቾቹ ቁጥር 8000 ሊደርስ ይችላል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ ባወጣዉ መግለጫ ግን የ2900 ሰዎች አስከሬን ማግኘቱን አስታዉቋል።አማፂዉ ቡድን ጎማን ከተቆጣጠረ በኋላ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፤ እስረኞች ተለቅቀዋል፣ የመንግስት፣ የድርጅቶችና የግል ንብረቶች ተመዝብረዋል።ጦርነቱ ዛሬም በተለይ ኖርድ ኪቩ በተባለዉ ግዛት መቀጠሉ ተዘግቧል።(DW)
@Ethionews433 @Ethionews433