ቴል አቪቭ-ሐማስ ከሚለቃቸዉ ታጋቾች አንዱ ኢትዮጵያዊ-እስራኤላዊ ነዉ
እስራኤልና ምዕራባዉያን መንግሥታት በአሸባሪነት የሚወነጅሉት የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሐማስ በቅርቡ ከሚለቃቸዉ ታጋቾች አንዱ ኢትዮጵያዊ-እስራኤላዊ ነዉ። እስራኤልና ሐማስ ባለፈዉ ጥር ባደረጉት ሥምምነት መሠረት በመጀመሪያዉ ዙር ከተለቀቁና ከሚለቀቁ ታጋቾች 6ቱ በመጪዉ ቅዳሜ ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሥድስቱ ታጋቾች አንዱ ኢትዮጵያዊ-እስራኤላዊ አቬራ መንግሥቱ ነዉ።አቬራ መንሥቱ እንደ ሌሎቹ ታጋቾች ሐማስ መስከረም 29፣ 2016 ደቡባዊ እስራኤልን በወረረበት ወቅት የታገተ አይደለም።ጀሩሳሌም ፖስት የተባለዉ የእስራኤል ጋዜጣ ምንጮችን ጠቅሶ ባለፈዉ ጥር በኢንተርኔት እንደዘገበዉ የ38ት ዓመቱ ጎልማሳ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር መስከረም 7፣2014 በራሱ ፈቃድ ጋዛ ገብቶ እጁን ለሐማስ ሰጥቷል።በዘገባዉ መሠረት ያኔዉ የ28 ዓመት ወጣት የእስራኤል ወታደር እንደነበር ሐማስ አስታዉቋል።ይሁንና ሑዩማን ራይትስ ወች የተባለዉ የመብት ተሟጋች ድርጅትና ቤተሰቦቹ የሐማስን አባባል አልተቀበሉትም።ወጣቱ የአዕምሮ ሕመምተኛ ነዉ ይባላል።ጋዛ ከመግባቱ በፊት ከእናቱ ጋር ተጣልቶ እንደነበረም ጋዜጣዉ የመብት ተሟጋቹን ድርጅት ጠቅሶ ዘግቧል።(DW)
@Ethionews433 @Ethionews433