በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ፤ ፋና እና የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት የሰሩት ዘገባዎች የተሳሳቱ ናቸዉ አሉ
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር የትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ኪሮስ ግዑሽ ፋና እና የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት የሰሩት ዘገባዎች የተሳሳቱ ናቸዉ አሉ።
መንግስታዊ የሆኑት የሚዲያ ተቋማቱ በትግራይ አዲሱን የትምህርት ስርዓት ለመተግበር የሚያግዙ መጽሃፍት ህትመት ዝግጅት ተጠናቋል ብለዉ ነበር።
የትምህርት ቢሮዉ ሃላፊ ግን በፌስቡክ ገጻቸዉ ላይ በበጀት እጥረት ምክንያት የመጽሐፍቱ ህትመት ዝግጅት አልተጀመረም ማለታቸዉን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።
ሃላፊዉ እንደዚህ አይነት የተዛባ መረጃ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዘብ ለማሰባሰብ የምናደርገውን ጥረት ያደናቅፋል ያሉም መሆኑን ዳጉ ጆርናል የታዘበ ሲሆን በሚዲያ ተቋማቱ የተሰሩ ዘገባዎች እንዲታረሙም ጠይቀዋል።
በበረከት ሞገስ
@Ethionews433 @Ethionews433