ወጣቱ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት - ቸርነት ሀሪፎ
ወጣቱ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ቸርነት ሀሪፎ በተባበሩት መንግሥታት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) ቋሚ ተወካይ ሆኖ ተሹሟል፡፡
በ20ዎቹ መጀመሪያ ዓመታት ዕድሜው በዲፕሎማትነት የተሾመው ቸርነት ሀሪፎ፤ የሹመት ደብዳቤውን ለመንግሥታቱ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አቅርቧል።
ዲፕሎማቱ ፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ምሥራቅ አፍሪካን ለመወከል በመብቃቴ ኩራት ይሰማኛል ሲል በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ የተሰማውን ደስታ አጋርቷል፡፡
የ23 ዓመቱ ቸርነት ሀሪፎ ሹመቱን ተከትሎ ከተለያዩ አካላት ከፍተኛ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።
የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁም (ዶ/ር)፥ ለቀጣናው ትብብር ያለህ ተነሳሽነት ሁላችንንም የሚያነሳሳ ነው በማለት ለወጣቱ ዲፕሎማት ስኬታማ የሥራ ጊዜን ተመኝተውለታል።
በኃይለማርያም ተገኝ
@Ethionews433 @Ethionews433