አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሳለጠ የጉምሩክ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል በርካታ የድጋፍ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ
******************************************
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም )
የጉምሩክ ኮሚሽን ተለያዩ አምራች ድርጅቶች እና ማህበራት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዝዘው ጫኔ፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሳለጠ የጉምሩክ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል በርካታ የድጋፍ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የድጋፍ ስራዎችን ለማጠናከር ተከታታይ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ በቀጣይም የተጀመረውን ቅንጅታዊ ስራ በማጠናከር ሀገር ከዘርፉ የምትጠብቀውን ውጤት ማምጣት ይገባልም ብለዋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ሙሉወርቅ ደረሰ በበኩላቸው፣ አምራች ዘርፉ አሁን ካለበት ችግር እንዲወጣ ለማስቻል መንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የአምራች ዘርፉን ለመደገፍ ባለፉት ወራት የተሰሩ ስራዎች እና ያጋጠሙ ችገሮችን የሚዳስስ የመነሻ ጹሁፍ በአምራች እና ወጪ ንግድ እቃ አሰራር እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወ/ሮ ገነት አብርሀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት የጉምሩክ ኮሚሽን ዘርፉን ለማሳደግ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ እና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላትም ተምሳሌት የሚሆን ነው ብለዋል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission