አሜሪካ ለሶማሌላንድ ዕውቅና በመስጠት “ቀዳሚዋ ሀገር ትሆናለች” የሚል ተስፋ እንዳላቸው የራስ ገዟ መሪ ተናገሩ
አሜሪካ ለሶማሌላንድ ዕውቅና የምትሰጥ “የመጀመሪያዋ ሀገር ትሆናለች” የሚል ተስፋ እንዳላቸው የራስ ገዝ አስተዳደሯ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዲላሒ ተናገሩ።
አዲሱ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፤ ሶማሊያ “ግዛቴ ናት” ለምትላት ሶማሌላንድ ዕውቅና ከሰጠ ሌሎች ሀገራት ይከተላሉ የሚል እምነት እንዳላቸውም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
አዲሱ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ይህን ያሉት፤ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 4፤ 2017 በዱባይ በተካሄደ የዓለም የመንግስታት ጉባኤ ውይይት ላይ ነው።
አብዲራህማን ኢሮ በሚል ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት አዲሱ ፕሬዝዳንት የዛሬ ሶስት ወር ገደማ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው አስቀድሞ፤ ለሶማሌላንድ ዕውቅና በመስጠት ቀዳሚዋ ሀገር ትሆናለች የሚል ተስፋ የተጣለው በኢትዮጵያ ላይ ነበር።
ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ስምምነት” የተፈራረሙት የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሒ አብዲ፤ ውሉ ተግባራዊ ሲሆን “ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ ዕውቅና እንደምትሰጥ” በይፋ መናገራቸው ለዚህ ተስፋ በማስረጃነት ሲጠቀስ ቆይቷል።
የሶማሌላንድ ልሂቃን ከፍተኛ ተስፋ የሰነቁበት የኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባር ሳይቀየር ቢዘገየም፤ የራስ ገዝ አስተዳደሯ አጥብቃ የምትሻውን ዕውቅና ከአሜሪካ ልታገኝ እንደምትችል ለትራምፕ አስተዳደር ቅርበት ያለው ተቋም ከወር በፊት ጥቆማ ሰጥቶ ነበር።
አዲሱ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት በዛሬው የዱባይ ጉባኤ ላይ ይህንኑ የሚያጠናክር አስተያየት አንጸባርቀዋል።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15030/