ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ አመት ብቻ 32.8 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዘገቡን ገለጸ
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፈው ግማሽ ዓመት 61.9 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። በዚሁ ጊዜ ውስጥ 32.8 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዘገቡን የገለጸው ተቋሙ፤ የደንበኞቹን ቁጥር 80.5 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉንም ይፋ አድርጓል።
ይህ የተገለጸው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ፍሬሕይወት ታምሩ፤ የተቋማቸውን የግማሽ አመት አፈጻጸም ዛሬ ረቡዕ የካቲት 5፣ 2017 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል ባቀረቡበት ወቅት ነው። ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት ለማግኘት ያቀደው አጠቃላይ ገቢ 163.7 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ባለፈው መስከረም አስታውቆ ነበር።
መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያ በመንፈቅ ዓመቱ ያገኘው ገቢ፤ ከእቅዱ 90.7 በመቶ ያሳካ መሆኑን አመልክቷል። ኩባንያው በዚሁ ወቅት ያስገባው ገቢ፤ በ2016 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ19 ቢሊዮን ብር ጨምሯል።
ኢትዮ ቴሌኮም ለገቢው መጨመር በምክንያትነት ከጠቀሳቸው ውስጥ፤ የሞባይል ስልክ ደንበኞቹ የዳታ እና የድምጽ አጠቃቀም ማደግ ይገኝበታል። የኩባንያው ደንበኞች የዳታ አጠቃቀም፤ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ሲነጻጸር በ48.8 በመቶ እድገት ያስመዘገበ መሆኑ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተጠቅሷል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)