ህገ-ወጥ ሎተሪ የሚያጫውቱ ተቀጡ
አዲስ አበባ ውስጥ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የህገ-ወጥ ሎተሪ ሲያጫውቱ በተገኙ ግለሰቦች ላይ የእስረትና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነባቸው፡፡
የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት አዲስ ከተማ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም፣ መስከረም 3 እና 5 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሶስቱ ግለሰቦች ላይ በእያንዳንዳቸው ላይ በሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ፣ የአንድ ዓመት ከስምንት ወር እስራትና ከ2,500 እስከ 18,000 ብር የገንዘብ ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ የፀና ፈቃድ ሳይኖር የሎተሪ ጨዋታ ማጫወት የሚከለክሉትን አንቀጾች በመጣሳቸው በፈፀሙት ወንጀል አቶ ዘውዱ ውባለም ወረታ አንድ ዓመት ከስምንት ወር እስራትና ብር 18,000 ብር፣ አቶ ሽኩር ወርቁ ደረጀ አንድ ዓመት ከስምንት ወር እስራትና ብር 2,500 ብር እንዲሁም አቶ ማሙሽ ደሬሎ ጫላ አንድ ዓመት ከስምንት ወር እስራትና ብር 2,500 ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ በህገወጥ የሎተሪ አጫዋቾች ላይ የሚተላለፉ የፍርድቤት ውሳኔዎችን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡