የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች መንግስት የ60 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሰጠ
በኢትዮጵያ ለዐይነ ስውራን ትምህርት መሠረተ ልማት የሚውል የ60 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ዛሬ የካቲት 8 ቀን 2017 ዓም መሰጠቱ ታወቀ።
ድጋፉ የተሰጠው የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ፕሬዚደንት ሼክ ሞሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በሰጡት መመሪያ ሲሆን የድጋፍ ስምምነቱን ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር መደረጉም ታውቋለል።
ድጋፉ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬስት መንግሥት ዓለማቀፍ በጎ አድራጎት ተግባራትን ለማስተባበር በዘረጋው ማዕቀፍ፣ ኧርዝ ዛይድ ፊላንትሮፊስ (Erth Zayed Philanthropies) ሥር የሚተገበር ኾኖ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በትብብር የሚፈጸም ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት እ ኤ አ.ሜይ 2024 በአዲስ አበባ ተመርቆ በይፋ ሥራ የጀመረው ሼክ ፋቲማ ቢንት ሙባረክ የዓይነ ሥውራን ትምሕርት ቤትን ስኬታማ ጅማሮና ተሞክሮ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የድጋፍ ሰነዱን የካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ፋውንዴሽን ዳይሬክተር ሚስተር ሞሐመድ ሐጂ አልኩሪ ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምኒስትር ደኤታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያንና የኧርዝ ዛይድ ፊላንትሮፊስ የበላይ ጠባቂ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ አሊ(ዶ/ር) በተገኙበት ተፈርሟል።
1.2 ሚሊዮን ዜጎች የማየት ውሱንነትን በሚያስከትሉ የጤና እክሎች በተጠቁባት፤ ከነዚህም መካከል 332,000 ዓይነ ሥውራን ድጋፉ በተለይ የትምሕርትና የጤና አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ባልተዳረሰባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ያለውን ሰብዓዊ ችግር ለመቅረፍ እንደሚያስችል ተገልጿል።
መሠረታዊ አገልግሎት በበቂ ሁኔታ በማይገኝባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን የሚያጠቃው ነገር ግን በሕክምና ሊድን በሚችለው ትራኮማ በሽታ የተጠቂዎች ቁጥር ኢትዮጵያ ከዓለም ከቀዳሚዎቹ ተርታ ትገኛለች።
በትምሕርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የአዳዲስ የልዩ ፍላጎት ትምሕርት ቤቶች ግንባታ እንዲከናወን ዕቅድ የተያዘ ሲኾን፣ በዘመናዊ መርጃ መሣሪያዎች የሚደራጁ፣ሙያ-ተኮር ሥርዓተ-ትምሕርት የሚዘጋጅላቸው ኾነው፣ ዓይነ ሥውራን ተማሪዎችን በክኅሎትና በዕውቀት በማብቃት ለከፍተኛ ትምሕርትና የሥራ ዓለም የሚያዘጋጁ የልኅቀት ማዕከላት በመኾን ያገለግላሉ ተብሏል።
ሼክ ጣይብ ቢን ሞሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን (Sheikh Theyab bin Mohamed bin Zayed Al Nahyan)እንደተናገሩት“አገራችን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ እጇን ትዘረጋለች። በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዓይነ-ሥውራን እና የዓይን ጤናቸው ለታወከ ተማሪዎች የምናደርገው ይህ ድጋፍ የዚህ ማሳያ ነው። ዓላማችን እነዚህ መሠረታዊ አገልግሎት የተጓደለባቸው ተማሪዎች በተሻለ ከባቢ ተምረው፣ የተሻለ ትምሕርት አግኝተው ሕልማቸውን ዕውን እንዲያደርጉ ማገዝ ነው። በአገራችንና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን መልካም የትብብር መንፈስ ይህ ጅማሬ ፍሬያማ እንደሚያደርገው እምነታችን ከፍ ያለ ነው።” ብለዋል።
ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን (Sheikh Shakhbout bin Nahyan Al Nahyan) በበኩላቸው “ዘላቂ ልማትና ስትራቴጂያዊ ትብብር ለዘላቂ ለውጥ መሠረት እንደኾኑ እንደ ሀገር ቀድመን ተረድተናል።ይህም ድጋፍ ማኅበረሰቦችን ከችግር ለማላቀቅ፣ ኢኮኖሚው ዕድሎችን እንዲፈጥር ለማስቻልና መሠረታዊ አገልግሎትን ለዜጎች ለማዳረስ ያለን ቁርጠኛ አቋም ማሳያ ይኾናል።ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያለን ትብብርም የአፍሪካ አገራት ትምሕርት ወጣቶችን ማብቂያና ዘላቂ ልማትን ማሳለጫ መኾኑን ተረድተው በትምሕርት ልማት ላይ እንዲያተኩሩ ያለንን የትኩረት አቅጣጫ ይገልጽልናል" ብለዋል።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በበኩላቸው “የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ መንግስት ጥራት ያለው ትምሕርትን ለሁሉም ዜጎቻችን ለማዳረስ የያዝነውን ግብ ለማገዝ የተደረገልን ድጋፍ በመንግሥታችንና በኢትዮጵያውያን ስም ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ። ይህ ድጋፍና አጋርነት ዓይነ-ሥውራን ተማሪዎች ተገቢና በቂ ዕድሎችን አግኝተው ስኬታማ እንዲኾኑ ከማገዙም በላይ ሁሉን-ዐቀፍ ማኅበረሰባዊ ዕድገት እንድናመጣ ትልቅ ግምት የምንሰጠው ድርሻ አለው” ብለዋል።
የካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ፋውንዴሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ሞሀመድ ሀጅ አልኩሪ በበኩላቸው፣ “ትምሕርት መሠረታዊ የሰው ልጆች መብት ነው። ልጆችም ልዩ ፍላጎቶቻቸው ተሟልተውላቸው የመማር ዕድል ሊመቻችላቸው ይገባል። የትምሕርት መሠረተ ልማትና ሥርዓተ ትምሕርትን በማሻሻል አካታችና ሁሉን ጠቃሚ ልማት እንዲመጣ መሠረት በመጣል ላይ ነን። ይህም ድጋፍ ትምሕርት ለትውልዶች የዕድልና የዕድገት ምንጭ ለመኾኑ ማሳያ ከመኾኑ ባሻገር ዓለማቀፍ ትብብር ለዘላቂ ለውጥ ያለውን ትልቅ ሚና በድጋሚ የሚያረጋግጥ ነው” ብለዋል።