#AAU
ራስ ገዝ የሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚተመነው ክፍያ ማህበረሰቡ ላይ ጫናን በማይፈጥር መልኩ ሊሆን እንደሚገባው ተጠቆመ
በኢትዮጵያ በቅርቡ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ መወሰኑን ተከትሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀዳሚውን የራስ ገዝነት ደረጃ በመያዝ በዘንድሮ ዓመት የመማር ማስተማሩን ስራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ለትምህርት መርሃ ግብሮቹ ያወጣውን ገንዘብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ሃሳባቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የሰጡ የትምህርት እና የህግ ባለሙያዎች ምንም እንኳን ተቋሙ ራሱን በራሱ ቢያስተዳድርም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያማከለ አሰራር ሊኖረው እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
መነሻውን ከሌሎች ሀገራት ያደረገው ይህ የራስ ገዝነት አካሄድ ብዙ ውዝግቦች የነበሩበት መሆኑን የገለፁት የትምህርት ባለሙያው ዶ/ር መክብብ ጣሰው ነገር ግን ከሃይማኖቱም ሆነ ከፖለቲካ ጫና በመላቀቅ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ባሻገር ድርጅቶች እና ባላሃብቶች እንደሚደግፉ በመግለፅ በኢትዮጵያም ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ መሆናቸው የሚበረታታ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ነገር ግን በክፍያው ከሌሎች ሀገራት ያለውን ተሞክሮ መውሰድ ካልተቻለ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይገልጻሉ፡፡
ይህንኑ ሀሳብ የሚጋሩት የህግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ትምህርት ማህበራዊ አገልግሎት ከሚባሉት ውስጥ እንደመሆኑ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ መንገድ ሊቀርብ ይገባል ባይ ናቸው፡፡ ትምህርት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሊቀርብ ይገባል ያሉት አቶ ጥጋቡ አግላይ እንዳይሆኑ በህግ ማዕቀፍም ሊኖራቸው እንደሚገባ ይጠቁማሉ፡፡
አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ትምህርት በነፃ በመንግስት በኩል ሊቀርብ የሚገባ መሰረታዊ ጉዳይ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን የገለፁልን ደግሞ የህግ ባለሙያው አቶ አይናለም ጌታሁን ናቸው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ደረጃም ወጪ መጋራት(ኮስት ሼሪንግ) የማስተማር አግባብ እንዳለ በመጥቀስ አሁን ላይ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው የተቀመጠው የገንዘብ ተመን ምናልባትም ከሚያወጣቸው ወጪዎች ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል የሚል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው እስኪቸገር ድረስ የማስከፈል ሂደት ካለ እና ሌሎችም ነገ ላይ ራስ ገዝ ሲሆኑ በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ ትምህርቱ ወደ ንግድነት የሚቀየር ይሆናል ሲሉ ያላቸውን ስጋት አቶ አይናለም ያስቀምጣሉ፡፡
ትምህርትን በጥራት ማድረስ በሚል ብቻ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያላማከሉ እርምጃዎች እንዳይወሰዱ በመንግስት በኩል ቁጥጥር ሊደረግባቸው እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ (መናኸሪያ ሬዲዮ)
⭐ For ExitExam Questions 👇
@Exit_Exam_Questions
@Exit_Exam_Questions
⭐ትምህርት ሚኒስቴር
@Ethiopian_Minister_Of_Education
@Ethiopian_Minister_Of_Education
🔺🔹🔺🔹🔺🔹🔺🔹🔺🔹