#AASTU
የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ በማድረግ የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃቸው አለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲኖረው እየሰራሁ ነው ያለው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፤ በሰባት ወር ጊዜ ውስጥ እውቅና የማግኘት ሂደቱ ይጠናቀቃል ብሏል፡፡
ዩኒቨርስቲው በአለም አቀፍ መስፈርት ከልሼዋለሁ ባለው የትምህርት ሥርዓት ያስተማራቸው የመጀመርያ ዙር ተማሪዎችም አስመርቆ ወደ ስራ ማስገባቱንም ሰምተናል፡፡
#የአዲስ_አበባ_ሳይንስና_ቴክኖሎጂ_ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ደረጄ እንግዳ(ዶ/ር) ከ2019 ጀምሮ ዩኒቨርስቲው ይህን እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን ስራ ሲሰራ ነበር ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡
እንደ ማሳያነት ያነሱት የትምህርት ካሪኩለም ክለሳ ማድረግ አንዱ ሲሆን በዚህ ሥርዓት ያለፉ ተማሪዎች ከባለፈው ዓመት ጀምሮ መመረቅ ጀምረዋል በማለት ነግረውናል፡፡
አለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት ባለፈው ሳምንት ግምገማ የሚያካሄድ ቡድን መጥቶ ስራውን አከናውኗል ያሉት ደረጄ እንግዳ(ዶ/ር) በመጀሪያው ሪፖርታቸውም አብዛኛዎቹ የትምህርት ክፍሎች ይህንን እውቅና እንደሚያሟሉ ተነግሮናል ብለዋል፡፡
ነገር ግን አንዳንድ ስራዎች በአንድ ወር ውስጥ እንድናስተካክል ተነግሮናል ያሉት የአስቱ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዩኒቨርስቲው የተነሱ ችግሮችን ለማስተካከል እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ውጤቱም ከ7 ወር በኋላ ሐምሌ ውስጥ ይታወቃል መባሉን ሰምተናል፡፡
እውቅናው ሲገኝ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የተመረቁ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃቸው በየትኛውም ተቋም አለም አቀፍ ተቀባይነት ይኖረዋል ተብሏል፡፡
[ዘገባው የሸገር ራዲዮ ጣቢያ ነው]
⭐ For ExitExam Questions 👇
@Exit_Exam_Questions
@Exit_Exam_Questions
⭐ትምህርት ሚኒስቴር
@Ethiopian_Minister_Of_Education
@Ethiopian_Minister_Of_Education
🔺🔹🔺🔹🔺🔹🔺🔹🔺🔹