ረጅም ጊዜ ያገለገሉና በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን በኤሌክትሪክ መኪኖች ለመተካት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ‼️
የቢሮው ኃላፊ ያብባል አዲስ በከተማዋ ለከፍተኛ የካርበን ልቀት ምክንያት ከሆኑት መካከል ያረጁና በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንደሚሰለፉ ተናግረዋል፡፡
በዚህም በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየሩ ጉዳይ በፌዴራል መንግስትም ሆነ በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው አብራርተዋል፡፡
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከአካባቢ ብክለት የፀዳና ደህንነቱ የተረጋገጠ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ያስችላሉ ብለዋል፡፡
አሁን ላይ በከተማዋ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የህዝብ ትራንስፖርቶች ወደ አገልግሎት መግባታቸውን ገለጹት ኃላፊው ይህ ተሞክሮ እየሰፋ የሚሄድና የግል መኪኖችንም የሚጨምር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የትራፊክ አደጋን ለመቀነስና ደህንነቱ የተረጋገጠ የትራንስፖርት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ "ሞተር አልባ" ወይም የእግረኛና የብስክሌት ትራንስፖርትን ማሳለጥ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
በከተማው የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ለእግረኛና ለብስክሌት መንገድ ቅድሚያ ሰጥተው መገንባታቸውን ማመላከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ቢሮው የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ፍላጎት ለማርካትና የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የአውቶብስና የባቡር አገልግሎቱን ለማስፋፋትና ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
Source: seleda
@Ethiopianbusinessdaily