ወጋገን ባንክ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ላይ በቀዳሚነት የተመዘገበ ኩባንያ ሆነ
ወጋገን ባንክ አክሲዮኑን በማስመዝገብ ወደ ገበያ ለማውጣት የሚያስችለውን ታሪካዊ እርምጃ መዉሰድ ችሏል።
ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ባዘጋጀው የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ይፋዊ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ ሲሆን በዚህም በገበያው ላይ በቀዳሚነት የተመዘገበ ኩባንያ መሆን መቻሉን አረጋግጧል።
ባንኩ በኢትዮጵያ በገበያው ላይ በመመዝገቡ ከተለምዷዊ የአክሲዮን መሸጫ ዘይቤዎች ወደ ዘመናዊ እና ቴክኖሎጂ ተኮር አማራጮች በመሸጋገር ተጨማሪ ካፒታል ለመሰብሰብ እንደሚያስችለዉ አስታውቋል።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily