ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማድረግ ስታደርግ የነበረችውን ድርድር አጠናቃ ከስምምነት ላይ ደረሰች
በዚህ የኃይል ሽያጭ ሥምምነቱ መሰረት በሀገራቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፀድቆ ከሚያዝያ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን በሥምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ 100 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ታከናውናለች ተብሏል።
ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ጋር የኃይል ሽያጭ እንዲሁም ኬንያ ከታንዛንያ ጋር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የኪራይ ውል በዛሬው ዕለት መፈራረማቸውን ካፒታል ሰምታለች።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህግ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ መርክነ እንደተናገሩት የሦስትዮሽ ሥምምነቱ ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችላትን መብት የሚሰጣት መሆኑንም መሆኑን አስረድተዋል።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily