አሊባባ በኢትዮጵያ በብር ክፍያ ከነገ ጀምሮ መቀበል ሊጀም መሆኑን አሳወቀ
አለም አቀፉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም አሊባባ፣ ከሰኞ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ በብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀመር አሳዉቋል።
ይህ እርምጃ ኢትዮጵያውያን በአሊ ኤክስፕረስ ላይ በቀላሉና በአገር ውስጥ ገንዘባቸው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል።
አሊባባ ይህን ውሳኔ የወሰነው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች ይበልጥ ተደራሽ ለመሆንና በዓለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና የውጭ ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ በማሰብ ነው ተብሏል። ይህ እርምጃ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ምክንያት ለአፍሪካውያን ትልቅ እንቅፋት የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ያለመ መሆኑም ተሰምቷል።
ይህም ማለት አሁን ኢትዮጵያውያን በአሊ ኤክስፕረስ ላይ የተለያዩ እቃዎችን ሲገዙ በብር ገንዘባቸው ክፍያ መፈጸም ይችላሉ። አሊባባ ይህን ለማሳካት በኢትዮጵያ ካሉ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ትብብር መፍጠሩን አስታውቋል።
Source: addisfortune
@Ethiopianbusinessdaily