⚡️ቢሮው ለተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች ወርሃዊ ቫት የማሳወቂያ ጊዜ ላይ አዲስ አሰራር መዘርጋቱን አስታወቀ
የተዘረጋው አሰራር ቀደም ሲል የነበረ ከፍተኛ የግብር ከፋዮች እንግልትና መጨናነቅ ለመቅረፍ የሚያስችል ነውም ተብሏል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በተጨማሪ እሴት ታክስ አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻልና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ከ62 ሺህ በላይ የሚሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች ግብራቸውን በሚሳወቅ አገልግሎት የሚያገኙበት አዲስ አሰራር ስርዓት መዘርጋቱ ተገልፆል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ከ62 ሺህ የሚበልጡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች መኖራቸው ቢሮው የገለፀ ሲሆን አብዛኞቹ የቫት ተመዝጋቢዎች ወራዊ ቫታቸውን የሚያሳውቁት በወሩ የመጨረሻ ቀናት መሆኑ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል ብሏል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ነባሩ አሰራር በመጨረሻ ቀናት ላይ ከሚፈጠር ከፍተኛ መጨናነቅና የኢንተርኔት መቆራረጥ የተነሳ ግብር ከፋዩን ለእንግልት ብሎም ለቅጣት ሲዳርግ መቆየቱ ቢሮው ገልፃል፡፡
Read More
Source: seleda
@Ethiopianbusinessdaily