ጄኔራል ፃድቃን ገብረተንሳይ ‹‹የኢሮብ ማህበረሰብ እየጠፋ ነው›› ሲሉ ተናገሩ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ጄኔራል ፃድቃን በመቀሌ በተከናወነ አንድ መድረክ ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ‹‹በምስራቃዊ ትግራይ ዞን የሚገኘውን ጉሎማክዳን ጨምሮ ሀምሳ ሁለት የትግራይ ወረዳዎች በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ናቸው፡›› ብለዋል፡፡
ጨምረውም ‹‹በባድመ፣ በኩናማና በተወሰኑ የእገላ ወረዳዎች ህዝባችን ቋሚ የሆነ ጥቃትና ማስፈራራት እየደረሰበት ነው፡፡›› ያሉት ጄኔራሉ የኢሮብ ማህበረሰብ ደግሞ እየጠፋ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ውስጥ ሊሰማራ ነው የሚለውን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ደግሞ ‹‹ጊዜያዊ አስተዳደሩ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት መከላከያ ሰራዊቱ የአገሪቱን አለም አቀፍ ድንበር እንዲያስከብር ጠይቋል፡፡›› ካሉ በኋላ ይህ ማለት ግን በትግራይ ውስጥ መከላከያው በትግራይ ውስጥ እንዲሰማራ ማለት እንዳልሆነ አስታውቀዋል፡፡
መከላከያው የአገርን ድንበር የማስከበር ሀላፊነት የተሰጠው በፕሪቶሪያ ስምምነት መሆኑን ጠቅሰውም ይህን እንዲያስፈፅም ጥያቄ ማቅረባቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
#እውን_መረጃ