🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰1️⃣3️⃣
እዛው ተቀምጬ ጮኩኝ አለቀስኩኝ ግን ማንም አድማጭ አልነበረም ::
አይ ልዑሌ ቢያንስ መጥፎ ሴት ነሽ ለምን ተልከሰከሽ እንኳን ሳይለኝ ፊቱን አዙሮብኝ ሄደ።
ተግባሩ ከቃላቱ በላይ ነገረኝ ።
ልክ ካጠገቤ ተነስቶ ሲሄድ ከበፊቱ የበለጠ ልቤ ተሰበረ ሆዴን ባር ባር አለኝ ።።
ምናለ ወደቤቴ ስሄድ መኪና ገጭቶ በደፋኝ ብዬ ተመኘሁ ::
በቃ ቀጥታ ወደ ቤቴ ሄጄ ትንሽ ልብስl በፌስታል ነገር ይዤ ልውጣ ብይ አስፋልት ለአስፋልት እንደሰካራም እየተገላጀጅኩ ትንሽ ተራመድኩና ታክሲ ውስጥ ገብቼ ወደ ሰፈሬ ሔድኩ ::.
እቤት ስገባ ማዘር እቤት መጥታ ቡና እያፈላች አገኘኋት
እንዴ ማሚ እንዴት ቶሎ መጣሽ ዛሬ ስላት አይ ትንሽ ጨጓራዬን አሞኝ አስፈቅጄ መጥቼ ነው ያው ታውቂ የለ ማታ ያቺን ምስር ቀመሰች ብሎ እንዲሁ አዋለኝኮ::
ሲብስብኝ አስፈቅጄ መጣሁ አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው እንዲህ ግርጥት ያልሺው ደሞ አልቅሰሻል እንዴ ብላ ከተቀመጠችበት ወደኔ መጣችና እጄን ጎተት አድርጋ ሶፋ ላይ አስቀመጠችኝ::
ልጄ ከመቼ ጀምሮ ነው ከኔ መደበቅ የጀመርሽው እውነቱን ንገሪኝ የሆንሽውን አለችኝ::
ማም ምንም የለም ባለፈው ነግሬሽ የለ በሱ ምክንያት ነው በቃ ሌላ ምንም የለም ማም በጣም እንደተጨነቀች ከፊቷ ላ ማየት ችያለሁ ::
ወይ ለምን ሄደሽ ሁሉንም ፍርጥርጥ አድርገሽ አትነግሪውም ከዛ ቡሀላ አንቺም አትጎጂም ቁርጥሽን ታውቂያለሽ ልጄ እንዲህ ሆነሽ ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ ለ1 ደቂቃ ፊትሽ እንዲጠቁር አልፈልግም ታዉቂያለሽ እዚህ ምድር ላይ ለመኖሬ ምክንያቴ እናንተ ልጆቼ ናችሁ አሁን አንቺ ደርሰሻል ልጄ ወግ ማዕረግ እንድታሳይኝ እፈልጋለሁ ::
ከሰው እኩል እንድታደርጊኝ እፈልጋለሁ አለቺኝ እናቴ እንዲህ ስታወራ አሳዘነችኝ የምር ምናለበት የምትፈልገውን አድርጌ ባስደስታት ብዬ ተመኘሁ ::
ግን አልችልም ማክቤልን የበለጠ እንድጠላው አደረገኝ እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው ነገር ቢኖር እንደሱ የጠላሁት ሰው እዚህ ምድር ላይ እንደሌለ ነው::
ከማምጋ ትንሽ ካወራን ቡሀላ ወደ ክፍሌ ገባሁ እንደለመድኩት አልጋዬ ላይ ተዘርሬ ማሰብ ጀመርኩ ::
ልዑሌ ቢያንስ አንድ ቃል እንኳን አትሂጂ እንዲህ አታድርጊ ሳይለኝ ጥሎኝ መሄድ ለኔ ጭራሽ ምንም አይነት ስሜት እንደሌለው ነው ያረጋገጠልኝ::
በግማሹ ደስ ብሎኛል ቢያንስ ልዑሌ እኔን ስላጣ ምንም አይጎዳም አሁን የሚያስጨንቀኝ ሳቋን መልኳን ሞራሏን ደም ግባቷን ለኔ ሰጥታ እሷ የተጎሳቆለችውን እናቴን አንድ ነገር እንኳን ሳላደርግላት ሳልጠቅማት ጥያት መሄዴን ሳስብ ውስጤ ይቆስላል ::
ግን በቃ ቢያንስ ከወለድኩ ቡሀላ ሁሉንም ብነግራት ይሻለኛል ብዬ አሰብኩ ከወለድኩ ቡሀላ ተመልሼ እመጣለሁ እያልኩ ከራሴጋ ካወራሁ ቡሀላ ለናቴ ደብዳቤ ልፅፍላት አስቤ ወረቀትና እስክሪብቶ አዘጋጀሁ ግን ምን ብዬ ልጀምር ግራ ገባኝ ግን መፃፍ እንዳለብኝ ደሞ አቃለሁ መጀመሪያ በጣም እንደምወዳት ፃፍኩላ ሲቀጥል የሆነ ቀን በጣም እንደማኮራት ጥያት የሄድኩት ግድ ሆኖብኝ እሷን አንገቷን ላለማስደፋት ብዬ እንደሆነ ፃፍኩላት ከዛ በላይ ግን መቀጠል አቃተኝ ትራሴ ውስጥ አስቀምጬው ተኛሁ::
በጠዋት ተነስቼ ከዚህ ሰፈር እንደምጠፋ ወስኜ ጨርሻለሁ ::
ጠዋት ስነሳ ሰአቱ ለምሳ ሰዐት እየተቃረበ ነበር እናቴም የሰሞኑን ሁኔታ ካየች ቡሀላ ጠዋት እኔ ካልተነሳሁ እሷ መቀስቀስ አቁማለች።
ምናለበት ማታ አላርም ብሞላ ብዬ እየተነጫነጭኩ ተነስቼ ልብሶቼን ማስተካከል ጀመርኩ ቤት ውስጥ ማንም የለም እህቴም ትምህርት ቤት ሄዳለች ::
ብቻየን መሆኔ ለኔ ጥሩ እንደሆነ እያሰብኩ::............. ነፃነት ይሰጡኛል ብዬ የማስባቸውን ልብሶች ከተትኩ ከድሮም ቀጫጫ አለመሆኔ እርግዝናዬ ጭራሽ እንዳያስታውቅ አድርጎታል:: ልብሴን ከታትቼ ጨረስኩ ደብዳቤውን ፊት ለፊት ላይ በደንብ እንደሚታይ ካረጋገጥኩ ቡሀላ :
ቤቱን ዞር ዞር ብዬ ለመሰናበት ከክፍሌ ወጣሁ ምናልባት ተመልሼ እዚህ ቤት ላልመለስ : እችላለሁ ምናልባት እራሴን ላጠፋ እችላለሁ :
ብቻ የምወስነው ከዚህ ቤትና ከዚህ ሰፈር ርቄ ከሄድኩ ቡሀላ ነው ::
ለመጨረሻ ጊዜ የናቴን ፈገግታ ለማየት ፈለኩና ቤቱን አፀዳድቼ ቡናውን አቀራርቤ የሚገርም ምሳ ሰርቼ ጠበቋት ምሳ ልትበላ ቤት ስትመጣ ቤቱ ሁላ ፏ ብሎ ስታገኘው በጣም ደስ አላት ዛሬ ምን ተገኘ አለች እየሳቀች አረ እማዬ አንቺን ለማስደሰት ነዋ እኔኮ በጣም ነው እምወድሽ አልኳት የሰራሁትን ምሳ እያቀርብኩ እኔምኮ እወድሻለሁ ልጄ ብላ ግንባሬን ሳም አደረገችኝ።።
ከናቴጋ እየተጨዋወትን ወደ ስራ የመመለሻ ሰአቷ ደረሰና ተሰናብታኝ ሄደች።
እቃውን አጣጥቤ አነሳስቼ ስጨርስ ሰዐት ሳይ 8 ሰአት አልፏል ::
ብቻዬን ቤት ውስጥ ድምፅ እያወጣሁ አለቅሳለሁ ማንም አይዞሽ ያልፋል የሚለኝ የለም ::
አይገርምም እንደዛ ምትሳሳልኝ እናቴ እንኳን ይሄን ጭንቀቴን ልትካፈለኝ አትችልም ( ግርም ከሚለኝ ነገር አንዱ ለልጅ ከወላጆች በላይ የሚቀርብ ሰው ባይኖርም ግን ስናድግ አብዛኛውን ጭንቀታችንን አያውቁም ፍቅር ስንጀምር : ስናቆም : ስንጎዳ : ስለነገ ስንጨነቅ : ያፈቀርነው ድንገት ጎድቶን ትልቅ ህመም ውስጥ ገብተን ግን ሁሌም ለቤተሰብ እንደጤነኛ ልጆች ነን )
የኔ እናት እንኳን እስከአሁን ድረስ ሚስጥረኛዬ ገመና ሸፋኜ ነበረች
እኔ ግን ገመናዋን ልሸፍንላት የምትፈልጋትን አይነት ልጅ ልሆንላት አልቻልኩ እሷ ሰራተኛ እኔ የቤት እመቤት ሆኜ አረፍነው እሱም ሳይበቃ ሌላ ሸክም ልጨምርባት አልችልም
🔻ክፍል አስራ አራት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💗የፍቅር ማእበል💗