FMC Sport ፋና ስፖርት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


This is Fana Media Corporation’s (FMC) Sport official Telegram channel.
@Fanatelevision
@afanoromofana
@tigrignafana
For more updates please visit
https://fanamc.com/amharic/

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት አስተናገደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በሴኔጋል አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

ዋሊያዎቹ በባህር ዳር ስታዲየም ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረጉት የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 2ኛ ጨዋታ ድል አልቀናቸውም፡፡

በጨዋታው ኢብራሂም ምባዬ በ11ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ግብ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሸንፏል፡፡

በዚሁ ምድብ ሞዛምቢክ ሱዳንን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ያሸነፈች ሲሆን፤ ከሴኔጋል በግብ ክፍያ በመብለጥ ምድቡን በ4 ነጥብ መምራት ጀምራለች፡፡


ኢትዮጵያ 0 – 1 ሴኔጋል ፡ የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 እየተመራ የመጀመሪያውን አጋማሽ አጠናቅቋል፡፡

ዋሊያዎቹ ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ከሴኔጋል አቻቸው ጋር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን በባህርዳር ስታዲየም እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በጨዋታው ኢብራሂም ምባዬ 11ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ግብ በሴኔጋል መሪነት ሁለቱ ቡድኖች ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡


ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ ይፋ አድርጓል፡፡

ተጫዋቹ ያጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት በማድሪድ ደርቢ ጨዋታ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በዚህም ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ለሁለት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ በ7ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ መርሐ ግብር በአትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ 1 መሸነፉ ይታወሳል፡፡


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በዴንማርክ ኮፐንሃገን በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ልዑኩ ቡድኑ አዲስ አበባ ሲደርስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህንን ጨምሮ የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸውን ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከዓለም 2ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወቃል፡፡


በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል - አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል አሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ፡፡

ዋሊያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ሲያደርጉ የቆዩትን ዝግጅት አስመልክተው አሰልጣኙ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ በአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ሀዋሳ ከተሞች ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው፤ በማጣሪያው ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከተጫዋቾች ምርጫ ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ ተጫዋቾችን የመረጥነው ወቅታዊ ብቃታቸውን መሰረት አድርገን ነው ብለዋል።

በዝግጅት ወቅት ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን፣ ከሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የዝግጅት ጨዋታ ማድረጋቸውን የገለጹት አሰልጣኙ፤ ጠንከር ያሉ ተጨማሪ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ለማግኘት ብንሞክርም አልተሳካም ነው ያሉት።

እንደ አሰልጣኝ የማምንበት የጨዋታ ስልት ቢኖረኝም፤ አሁን ባለው ሁኔታ በየትኛውም የጨዋታ መንገድ ለማሸነፍ አቅደን ነው የተዘጋጀነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በመጪው አርብ በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ከሱዳን ጋር እንዲሁም በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ስታዲየም ይጫወታል።

በዳንኤል እንዳለ


ሉዊስ ዴላፎንቴ በስፔን ብሔራዊ ቡድን ውላቸውን አራዘሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ሉዊስ ዴላፎንቴ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያላቸውን ውል ለረጅም ዓመታት አራዝመዋል፡፡

በዚህም አሰልጣኝ ሉዊስ ዴላፎንቴ የስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው እስከ ፈረንጆቹ 2032 ድረስ የሚቆዩ ይሆናል፡፡

አሰልጣኝ ሉዊስ ዴላፎንቴ የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከ16 ዓመታት በኋላ የዓለም ዋንጫን እንዲያሳካ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

አሰልጣኙ በ2026 በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ የተካሄደውን የዓለም ዋንጫ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ማሳካታቸው አይዘነጋም፡፡

የአሰልጣኙን ውል ማራዘም ይፋ ያደረጉት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ራፋኤል ሎዛን እንዳሉት ዴላ ፎንቴ በስፔን ብሄራዊ ቡድን ታሪክ በጣም ስኬታማ ከሆኑት መካከል አንደኛው ነው፡፡

በዚህም እንደ ሀገር በመተማመን ላይ የተመሰረተ የተረጋጋ ፕሮጀክት ማስቀጠል እንፈልጋለን ብለዋል።

በሰለሞን በቀለ


ግራኒት ዣካ ከስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ታገደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል ግራኒት ዣካ ከብሔራዊ ቡድኑ ታግዷል፡፡

ግራኒት ዣካ በፈረንጆቹ 2022 የአርሰናል ተጫዋች በነበረበት ወቅት ማድረግ የሚጠበቅበትን ክትባት ሳያደርግ በሃሰት የኮቪድ ሰርተፍኬት ወስዷል በሚል መጠርጠሩን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

በዚህም የ33 ዓመቱ ተጫዋች ዣካ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን፤ የስዊዘርላንድ እግርኳስ ፌዴሬሽን አምበሉን ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጪ አድርጓል፡፡

ፌዴሬሽኑ ግራኒት ዣካ በቀጣይ በሚደረጉ የኔሽንስ ሊግ ሦስት ጨዋታዎች ላይ እንደማይሳተፍ በመግለጽ፤ ውሳኔው የጋራ ስምምነት ስለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አሁን ትኩረቱ በቀጣይ የሚደረጉ የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡


እግር ኳስን ለማቆም ጫፍ ደርሶ የነበረው ኮከብ – ራፊንሃ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የቢቢሲ ስፖርት አምደኛው ጊሌም ባላጌ፥ ብራዚላዊው ኮከብ “የእግር ኳስ ህልሜ አክትሞለታል” የሚል ውሳኔ ላይ የደረሰበትን አጋጣሚ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ይተርካል። በብራዚሏ ፖርቶ አሌግሪ ከተማ የተወለደው ራፋኤል ዲያዝ ቤሎሊ (ራፊንሃ) እግር ኳስን የጀመረው እንደ አብዛኞቹ ተጫዋቾች ለኳስ ባለው ፍቅር ብቻ አልነበረም። ስኬታማ እግር ኳስ ተጫዋች…

https://www.fanamc.com/archives/322935


የአርሰናል ያልተጠበቀው ሽንፈት


ከደቂቃዎች በኋላ በኤክስትራ ታይም ስፖርት ቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን

#ስፖርት_ፖድካስት
#ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን #fanapodcast #fanadigitalmedia #fanamediacorporation #PoodkaastiiFaanaa #fanadigitalmedia فانا_عربي_بودكاست


ማንቼስተር ዩናይትድና ፉልሃም አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር 1 አቻ ተለያይቷል፡፡

ምሽት12:30 ላይ በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፉልሃም ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ መምራት ችሎ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ማቲያስ ኩኛ በጨዋታው መገባደጃ ላይ ባስቆጠራት ግብ ማንቼስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋርቷል፡፡


የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሳያልፍ ቀረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣሪያ ጨዋታ በታንዛኒያ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሳያልፍ ቀርቷል፡፡

ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ ቡሩንዲ እና ዩጋንዳ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

የፍጻሜ ተፋላሚ የሚሆኑት ሁለት ብሔራዊ ቡድኖች ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ።


ሃሪ ኬን - በ98 ጨዋታዎች 100 ግቦች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሃሪ ኬን በጀርመን ቡንደስ ሊጋ አስደናቂ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡

በሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር በግብ አስቆጣሪነቱ የሚታወቀው ሃሪ ኬን ወደ ጀርመን ካቀና በኋላም በግብ አስቆጣሪነቱ ቀጥሏል፡፡

በ2023/24 የውድድር ዓመት ባየርን ሙኒክን የተቀላቀለው ሃሪ ኬን ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ዓመታት የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

የ33 ዓመቱ ተጫዋች ሃሪ ኬን ወደ ጀርመን ካቀና በኋላ በ98 የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ጨዋታዎች 100 ግቦችን በማስቆጠር አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

ዲተር ሙለር ከዚህ ቀደም በ129 የቡንደስ ሊጋ ጨዋታዎች 100 ግቦችን በማስቆጠር ክብረ ወሰኑን ይዞ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ሃሪ ኬን በ98 የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች 100 ግቦችን በማስቆጠር ክብረ ወሰኑን የግሉ አድርጓል፡፡


ሻምፒዮኑ አርሰናል በብራይተን 3 ለ 0 ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ብራይተን አርሰናልን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ፓስካል ግሮስ፣ ኮስቱላስ እና አንድሬስ አሰቆጥረዋል፡፡

ሻምፒዮኑ አርሰናል በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡

ብራይተን በዚህ የውድድር ዓመት በሊጉ ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች 16 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

በዚህም በ2026/27 የውድድር ዓመት እስካሁን በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚው ቡድን ነው፡፡


አስቶንቪላ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አስቶንቪላ ቶተንሃም ሆትስፐርን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ቀን 8 ሰዓት 30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የአስቶንቪላን የማሸነፊያ ግቦች ማንዛምቢ፣ ጃክሰን እና ቡንዲያ አስቆጥረዋል፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐርን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦችን ኮነር ጋላገር እና ቫንሄክ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር በውድድር ዓመቱ በሊጉ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች በአንዱም ማሸነፍ አልቻለም፡፡ በሦስቱ ተሸንፎ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል፡፡

አስቶንቪላ በበኩሉ በዚህ የውድድር ዓመት በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ማሳካት ችሏል፡፡

የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ አርሰናል ከብራይተን፣ ኤቨርተን ከኢፕስዊች ታውን እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ከሃል ሲቲ ይገናኛሉ፡፡

ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ኖቲንግሃም ፎረስት ከኮቨንትሪ ሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡


ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ሺህ ሜትር ሴቶች በዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ልቅና አምባው የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ፤ በርቀቱ የተሳተፈችው ሌላኛዋ አትሌት አለሺኝ ባወቀ 5ኛ ደረጃን አስመዝግባለች።

አትሌት ልቅና አምባው በውድድሩ 14:41 በመግባት ድንቅ ብቃቷን በማሳየት አሸንፋለች፡፡


በዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ የ1 ማይል ውድድር ፍሬወይኒ ኃይሉ 2ኛ ወጣች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ የሴቶች የ1 ማይል ውድድር ፍሬወይኒ ኃይሉ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች፡፡

በኮፐንሃገን፤ ዴንማርክ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር የሴቶች የ1 ማይል ውድድር ተካሂዷል፡፡

በውድድሩ ፍሬወይኒ ኃይሉ ፈረንሳዊቷን አጋቲ ጉሊሞት ተከትላ 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ስታሸንፍ፤ ብርቄ ሀየሎም 29ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡


ቼልሲ በብሬንትፎርድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ቼልሲን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የብሬንትፎርድን የማሸነፊያ ግቦች ጄደን አንቶኒ፣ ኢጎር ቲያጎ እና ፋቢዮ ካርቫልሆ አስቆጥረዋል።

ቼልሲ በውድድር ዓመቱ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።


አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ በሁለት ዓመታት ውል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።

Показано 18 последних публикаций.