አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ የነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢፌዲኤሪ ፕሬዝዳንት በመሆን ሳህለወርቅ ዘውዴን ተክተው ተሾሙ።
ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ አምባሳደር ታዬ ያለምንም ተቃውሞ፤ በአምስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ሹመቱ ጸድቆላቸው በምክር ቤቱ ፊትለፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለአዲሱ ተሻሚ አምባሳደር ታዬ ህገ መንግስቱን በማስረከብ ኃላፊነታቸውን አስረክበው በክብር ተሰናብተዋል።